ዘኍል 6:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በናዝራዊነትም ለማገልገል ራሱን እንደገና ለእግዚአብሔር የተለየ ያደርጋል፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሰው ጠጒሩ ከመርከሱ የተነሣ ከዚያ በፊት በናዝራዊነት የነበረበት ክፍለ ጊዜ አይቈጠርለትም፤ ስለ በደልም ለሚከፈለው ዋጋ አንድ ዓመት የሞላው የበግ ጠቦት ያምጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ራሱን የተለየ ያደረገበትን ጊዜ ለእግዚአብሔር መቀደስ አለበት፤ እንዲሁም የአንድ ዓመት ተባዕት ጠቦት የበደል መሥዋዕት አድርጎ ያምጣ። ያለፉት ቀኖች አይቈጠሩም፤ በተለየበት ጊዜ ረክሷልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራሱን የለየበትን ወራትም ለጌታ ይቀድሳል፥ የአንድ ዓመትም ተባት ጠቦት ለበደል መሥዋዕት ያመጣል፤ ናዝራዊነቱ ግን ረክሶአልና ያለፈው ወራት ሁሉ ከንቱ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በስእለቱ ወራትም ሁሉ ለእግዚአብሔር ይቀደሳል፤ የአንድ ዓመትም ተባት ጠቦት ለበደል መሥዋዕት ያምጣ፤ ስእለቱ ግን ረክሶአልና ያለፈው ወራት ሁሉ አይቈጠርለትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ራሱን የተለየ ያደረገበትን ወራትም ለእግዚአብሔር ይቀድሳል፥ የአንድ ዓመትም ተባት ጠቦት ለበደል መሥዋዕት ያምጣ፤ ናዝራዊነቱ ግን ረክሶአልና ያለፈው ወራት ሁሉ ከንቱ ይሆናል። |
“ነገር ግን ደግ ሰው መልካም ማድረጉን ትቶ ክፉ ሰዎች የሚያደርጉአቸውን ክፉና አጸያፊ ነገሮች ማድረግ ቢጀምር፥ በሕይወት መኖር የሚችል ይመስላችኋልን? አይደለም! እንዲያውም ያደረገው የደግነት ሥራ ሁሉ አይታሰብለትም፤ ባለመታመኑና ኃጢአተኛም በመሆኑ ምክንያት ይሞታል።
ስለ ሠራው ኃጢአት ለእግዚአብሔር የበደል መሥዋዕት ያምጣ፤ ይኸውም ከመንጋው የበግ ወይም የፍየል እንስት ይሆናል፤ ካህኑም ስለ ኃጢአቱ ያስተሰርይለታል።
“አንድ ሰው በግ ወይም ፍየል ማቅረብ ካልቻለ ግን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች፥ አንደኛይቱን ስለ ኀጢአት ለሚቀርብ መሥዋዕት፥ ሁለተኛይቱንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ የበደሉን ዕዳ ይከፍል ዘንድ ለእግዚአብሔር ያምጣ።
ካህኑም አንዱን ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት፥ ሌላውን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብ ናዝራዊው ሬሳ በመንካቱ ስለ ረከሰ ያስተሰርይለታል፤ በዚያኑ ቀን ናዝራዊው ጠጒሩን እንደገና ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ያደርገዋል።
ኢየሱስ ግን “የጽድቅን ሥራ ሁሉ በዚህ መንገድ መፈጸም ስለሚገባን፥ አሁንስ ተው፤ እንዲሁ ይሁን” ሲል መለሰለት። ዮሐንስም በነገሩ ተስማምቶ ኢየሱስን አጠመቀው።