ዘኍል 35:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው ሌላውን ሰው በብረት መሣሪያ እስኪሞት ድረስ ቢመታው ያ ሰው ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳዩም ይገደል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘አንድ ሰው ሌላውን እንዲሞት በብረት ቢመታው ነፍሰ ገዳይ ነው፤ በሞትም ይቀጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ማንኛውም ሰው ሌላውን ሰው በብረት መሣርያ እስኪሞት ድረስ ቢመታው ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳዩም ፈጽሞ ይገደል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በብረት መሣሪያ ቢመታው፥ ቢሞትም ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳዩም ፈጽሞ ይገደል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በብረት መሣርያ እስኪሞት ድረስ ቢመታው ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳዩም ፈጽሞ ይገደል። |