በዚህም መሠረት ድንበሩ ከሜዲቴራኒያን ባሕር ተነሥቶ እስከ ሐጻር ዔኖን፥ እርሱም በደማስቆና በሐማት ድንበር በስተሰሜን እስካለው ቦታ ድረስ ይደርሳል፤ ይህም የሰሜኑ ድንበር ነው።
ዘኍል 34:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ዚፍሮን ከተሻገረም በኋላ በሐጻርዔናን ይቆማል፤ ይህም የሰሜን ድንበራችሁ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስከ ዚፍሮን በመቀጠል መጨረሻው ሐጻርዔናን ይሆናል፤ በሰሜን በኩል ያለው ወሰናችሁ ይኸው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንበሩም ወደ ዚፍሮን ይዘረጋል መጨረሻውም ሐጸርዔናን ይሆናል፤ ይህ የሰሜን ድንበራችሁ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳርቻውም ወደ ዲፍሮና ያልፋል፤ መውጫውም አርሴናይን ይሆናል፤ በመስዕ በኩል ያለው ወሰናችሁም በዚህ ይሁናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳርቻውም ወደ ዚፍሮን ያልፋል እስከ ሐጸርዔናንም ድረስ ይወጣል፤ ይህ የሰሜን ዳርቻችሁ ይሆናል። |
በዚህም መሠረት ድንበሩ ከሜዲቴራኒያን ባሕር ተነሥቶ እስከ ሐጻር ዔኖን፥ እርሱም በደማስቆና በሐማት ድንበር በስተሰሜን እስካለው ቦታ ድረስ ይደርሳል፤ ይህም የሰሜኑ ድንበር ነው።
ምድሪቱን ለመካፈል የተመዘገቡት ነገዶች እነዚህ ናቸው፤ የዳን ነገድ በምድሪቱ ሰሜናዊ ወሰን አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ እርሱም ከሔትሎን ወደ ሐማት መግቢያ የሚወስደውን ጐዳና ተከትሎ ከዚያም ሐጻርዔኖንና የደማስቆ ሰሜናዊ ክፍል ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ የዳን ድንበር ይሆናል።