ዘኍል 3:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሜራሪ ወንዶች ልጆች ማሕሊናና ሙሺ ይባሉ ነበር፤ እነዚህም በየስማቸው የቤተሰብ አባቶች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሜራሪ ጐሣዎች፤ ሞሖሊና ሙሲ። እንግዲህ የሌዋውያን ጐሣዎች በየቤተ ሰባቸው ሲቈጠሩ እነዚህ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሜራሪም ልጆች በየወገኖቻቸው፤ ሞሖሊ፥ ሙሲ። የሌዋውያን ወገኖች በየአባቶቻቸው ቤቶች እነዚህ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሜራሪም ልጆች በየወገናቸው፤ ሞሐሊ፥ ሙሲ። የሌዋውያን ወገኖች በየአባቶቻቸው ቤቶች እነዚህ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሜራሪም ልጆች በየወገናቸው፤ ሞሖሊ፥ ሙሲ። የሌዋውያን ወገኖች በየአባቶቻቸው ቤቶች እነዚህ ናቸው። |
ገዳልያ፥ ጸሪ፥ ያሻያ፥ ሺምዒ፥ ሐሻብያና ማቲትያ ተብለው የሚጠሩት ስድስቱ የይዱቱን ልጆች ሲሆኑ እነርሱም በበገና ድምፅ እየታጀቡ በአባታቸው መሪነት የእግዚአብሔር መንፈስ ያቀበላቸውን መዝሙር እያሰሙ እግዚአብሔርን በዝማሬ ያከብሩና ያመሰግኑ ነበር።
ሥራውን እንዲቀጥሉ የተደረጉት ስማቸው ከዚህ በታች የተዘረዘረው ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፦ ከቀዓት ጐሣ፦ የዐማሣይ ልጅ ማሐትና የዐዛርያስ ልጅ ኢዩኤል፤ ከመራሪ ጐሣ፦ የዓብዲ ልጅ ቂሽና የይሀልኤል ልጅ ዐዛርያስ፤ ከጌርሾን ጐሣ፦ የዚማ ልጅ ዮአሕና የዮአሕ ልጅ ዔዴን፤ ከኤሊጻፋን ጐሣ፦ ሺምሪና ይዒኤል፤ ከአሳፍ ጐሣ፦ ዘካርያስና ማታንያ፤ ከሄማን ጐሣ፦ ይሒኤልና ሺምዒ፤ ከይዱቱን ጐሣ፦ ሸማዕያና ዑዚኤል።
የካህናት ሥራ ምድብ በጐሣ በጐሣ ሲሆን፥ ዕድሜአቸው ኻያ ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ሌዋውያን፥ የሥራ ምድብ ግን በሚያከናውኑት የሥራ ዐይነት የሚወሰን ነበር፤
ሌዊ ጌርሾን፥ ቀዓትና መራሪ የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነዚህም በየስማቸው የሌዊ ነገድ አባቶች ናቸው፤ ሌዊ በሕይወት የኖረበት ዘመን 137 ዓመት ነበር።