ዘኍል 3:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቀዓትም ወንዶች ልጆች ዓምራም፥ ይጽሐር፥ ኬብሮንና ዑዚኤል ይባሉ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀዓት ጐሣዎች፤ እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀዓትም ልጆች በየወገኖቻቸው፤ እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀዓትም ልጆች በየወገናቸው እንበረም፥ ይሳዓር፥ ኬብሮን፥ አዛሄል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀዓትም ልጆች በየወገናቸው፤ እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል። |
ቀጥሎም ዐሥራ አራቱ የሄማን ልጆች ሲሆኑ እነርሱም ቡቂያ፥ ማታንያ፥ ዑዚኤል፥ ሸቡኤል፥ ያሪሞት፥ ሐናንያ፥ ሐናኒ፥ ኤሊአታ፥ ጊዳልቲ፥ ሮማምቲዔዜር፥ ዮሽበቃሻ፥ ማሎቲ፥ ሆቲርና ማሕዚአት ናቸው፤
ሥራውን እንዲቀጥሉ የተደረጉት ስማቸው ከዚህ በታች የተዘረዘረው ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፦ ከቀዓት ጐሣ፦ የዐማሣይ ልጅ ማሐትና የዐዛርያስ ልጅ ኢዩኤል፤ ከመራሪ ጐሣ፦ የዓብዲ ልጅ ቂሽና የይሀልኤል ልጅ ዐዛርያስ፤ ከጌርሾን ጐሣ፦ የዚማ ልጅ ዮአሕና የዮአሕ ልጅ ዔዴን፤ ከኤሊጻፋን ጐሣ፦ ሺምሪና ይዒኤል፤ ከአሳፍ ጐሣ፦ ዘካርያስና ማታንያ፤ ከሄማን ጐሣ፦ ይሒኤልና ሺምዒ፤ ከይዱቱን ጐሣ፦ ሸማዕያና ዑዚኤል።
ሌዊ ጌርሾን፥ ቀዓትና መራሪ የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነዚህም በየስማቸው የሌዊ ነገድ አባቶች ናቸው፤ ሌዊ በሕይወት የኖረበት ዘመን 137 ዓመት ነበር።
ዓምራም ዮኬቤድ የተባለችውን የአባቱን እኅት አገባ፤ እርስዋም አሮንንና ሙሴን ወለደችለት። ዓምራም በሕይወት የኖረበት ዘመን 137 ዓመት ነው።