ከመጀመሪያው ጠቦት ጋር አንድ ኪሎ ግራም ምርጥ የሆነ የስንዴ ዱቄት ከአንድ ሊትር ተጨምቆ የተጠለለ የወይራ ዘይት ጋር ለውሰህ አቅርብ፤ አንድ ሊትር የወይን ጠጅም መባ አድርገህ አፍስስበት።
ዘኍል 28:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም የምግብ ቊርባን በተመሳሳይ ሁኔታ በሰባቱም ቀኖች ውስጥ ታቀርባላችሁ፤ ይህንንም የምታቀርቡት በቀኑ ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕትና የመጠጥ መባ ጋር ተጨማሪ በማድረግ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህም ዐይነት ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሆኖ በየዕለቱ ለሰባት ቀን በእሳት ለሚቀርብ መሥዋዕት የምግብ ቍርባን አዘጋጁ፤ ይህም ከመጠጥ ቍርባኑ ጋራ በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ጋራ ሆኖ በተጨማሪ ይቀርባል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርበውን የቁርባኑን ማዕድ ሰባት ቀን በየዕለቱ እንዲሁ ታቀርባላችሁ፤ ዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከመጠጡ ቁርባን ጎን ለጎን የሚቀርብ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን በእሳት የሚደረገውን ቍርባንና መሥዋዕት ሰባት ቀን በየዕለቱ እንዲሁ ታቀርባላችሁ፤ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከመጠጡ ቍርባን ሌላ ይቀርባል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚደረገውን የቍርባኑን መብል ሰባት ቀን በየዕለቱ እንዲሁ ታቀርባላችሁ፤ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከመጠጡ ቍርባን ሌላ ይቀርባል። |
ከመጀመሪያው ጠቦት ጋር አንድ ኪሎ ግራም ምርጥ የሆነ የስንዴ ዱቄት ከአንድ ሊትር ተጨምቆ የተጠለለ የወይራ ዘይት ጋር ለውሰህ አቅርብ፤ አንድ ሊትር የወይን ጠጅም መባ አድርገህ አፍስስበት።
በዓሉ በሚከበርባቸው ሰባት ዕለቶች በእያንዳንዱ ቀን ምንም ነውር የሌለባቸውን ሰባት ኰርማዎችና ሰባት የበግ አውራዎች በሙሉ ለሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የሚቀርቡትን ያዘጋጃል፤ ከዚህም ጋር በእያንዳንዱ ዕለት ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚሆን አንድ የፍየል አውራ ያዘጋጃል።
“ለእኔ የሚቀርበውም በእሳት የሚቃጠል የምግብ ቊርባን የሚከተለው ነው፦ በየቀኑ ለሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት አንድ ዓመት የሞላቸውና ምንም ነውር የሌለባቸው ሁለት የበግ ጠቦቶች ይሁኑ፤