ኤልያስም “የባዓልን ነቢያት ያዙ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ!” ሲል አዘዘ። ሕዝቡም በሙሉ ያዛቸው፤ ኤልያስም ወደ ቂሾን ወንዝ እየመራ ወስዶ በዚያ ሁሉንም ገደላቸው።
ዘኍል 25:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም ለእስራኤል መሪዎች “እያንዳንዳችሁ ከየነገዳችሁ በዓል ለሚባለው የፒዖር ጣዖት የሰገደውን ሰው ሁሉ ግደሉ” ብሎ ትእዛዝ አስተላለፈ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም የእስራኤልን ዳኞች፣ “እያንዳንዳችሁ በኣል ፌጎርን በማምለክ የተባበሩትን ሰዎቻችሁን ግደሉ አላቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም የእስራኤልን ዳኞች፦ “እናንተም እያንዳንዳችሁ ብዔልፌጎርን የተከተሉትን ሰዎቻችሁን ግደሉ” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም የእስራኤልን ሕዝቦች፥ “እናንተ እያንዳንዳችሁ ብዔል ፌጎርን የተከተሉትን ሰዎቻችሁን ግደሉ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም የእስራኤልን ዳኞች፦ እናንተ ሁሉ ብዔልፌጎርን የተከተሉትን ሰዎቻችሁን ግደሉ አላቸው። |
ኤልያስም “የባዓልን ነቢያት ያዙ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ!” ሲል አዘዘ። ሕዝቡም በሙሉ ያዛቸው፤ ኤልያስም ወደ ቂሾን ወንዝ እየመራ ወስዶ በዚያ ሁሉንም ገደላቸው።
በተጨማሪ ግን ችሎታ ያላቸውን ሰዎች መርጠህ በሕዝቡ ላይ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የኀምሳ አለቆችና የዐሥር አለቆች አድርገህ ሹም። እነርሱ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፥ እምነት የሚጣልባቸውና በጉቦም የማይደለሉ ሰዎች መሆን አለባቸው።
“በቅርብም ሆነ በሩቅ ካሉት፥ ከአንዱ የምድር ዳርቻ በአካባቢህ ካሉ ከአሕዛብ አማልክት አንተ ወይም አባቶችህ የማታውቁትን አንዱን እናምልክ በማለት ሌላ እንኳ ቀርቶ የአባትህ፥ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ፥ ወንድ ልጅህ፥ ወይም ሴት ልጅህ ወይም የምትወዳት ሚስትህ ወይም የቅርብ ወዳጅህ በምሥጢር ይገፋፋህ ይሆናል።
ያለ ማመንታት እንዲሞት አድርግ፤ ይልቁንም በእርሱ ላይ ድንጋይ በመወርወር የመጀመሪያ ሁን፤ ሌላውም ሁሉ ተባብሮ በድንጋይ ወግሮ ይግደለው።