ዘኍል 24:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትንቢቱንም እንዲህ እያለ መናገር ጀመረ። “ዐይኑ በግልጥ የሚያይለት፥ የቢዖር ልጅ በለዓም የሚናገረው የትንቢት ቃል ይህ ነው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እንዲህ ሲል ንግሩን ጀመረ፤ “የቢዖር ልጅ የበለዓም ንግር፤ የዚያ ዐይኑ የተከፈተለት ሰው ንግር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ “የቢዖር ልጅ በለዓም እንዲህ ይላል፥ ዐይኖቹ የተከፈቱለት ሰው እንዲህ ይላል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምሳሌም ይናገር ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ “የቢዖር ልጅ በለዓም እንዲህ ይላል፥ በትክክል የሚያይ ሰው እንዲህ ይላል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምሳሌውንም ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ የቢዖር ልጅ በለዓም እንዲህ ይላል፥ ዓይኖቹ የተከፈቱለት ሰው እንዲህ ይላል፤ |
በለዓምም እንዲህ ሲል ትንቢት ተናገረ፦ “የሞአብ ንጉሥ ባላቅ የምሥራቅ ተራራዎች ከሚገኙበት ከሶርያ ጠርቶ አመጣኝ። እርሱም ‘ና፤ የእስራኤልን ሕዝብ አውግዝልኝ፤ እንዲጠፉም ርገምልኝ’ አለኝ።
የግዚአብሔርን ቃል የሚሰማው ሰው የትንቢት ቃል ወድቆ ሳለ ዐይኖቹ ተከፍተው ሁሉን የሚችል አምላክን ራእይ የሚያይ ሰው መልእክት ይህ ነው።
ይህም የሆነበት ምክንያት በነቢይ እንዲህ ተብሎ የተጻፈው እንዲፈጸም ነው፦ “ንግግሬን በምሳሌ እገልጣለሁ፤ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውን እናገራለሁ።”