ዘኍል 23:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ እኔ እግዚአብሔር ያልረገመውን እንዴት እረግመዋለሁ? እግዚአብሔር ያላወገዘውንስ እንዴት አወግዛለሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ያልረገመውን፣ እኔ እንዴት ረግማለሁ? እግዚአብሔር ያላወገዘውንስ፣ እንዴት አወግዛለሁ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር ያልረገመውን እንዴት እረግማለሁ? ጌታስ ያላወገዘውን እንዴት አወግዛለሁ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ያልረገመውን እንዴት እረግማለሁ? እግዚአብሔርስ ያልተጣላውን እንዴት እጣላለሁ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ያልረገመውን እንዴት እረግማለሁ? እግዚአብሔርስ ያልተጣላውን እንዴት እጣላለሁ? |
የሐሰተኞች ነቢያትን ምልክቶችና፥ የሟርተኞችን ጥንቈላ ከንቱ አደርጋቸዋለሁ። የጥበበኞችን ዕውቀት እገለብጣለሁ፤ ዕውቀታቸውንም ወደ ሞኝነት እለውጠዋለሁ፤
የሕዝቡም ቊጥር ከእኛ እጅግ የበዛ ነው፤ ስለዚህ ወደዚህ መጥተህ እነርሱን ርገምልኝ፤ በዚህ ዐይነት ምናልባት ድል ልነሣቸውና ከምድሪቱ ላስወጣቸው እችል ይሆናል፤ አንተ የምትመርቀው የተመረቀ፥ አንተም የምትረግመው የተረገመ እንደሚሆን ዐውቃለሁ።”
በያዕቆብ ልጆች ላይ ምንም ዐይነት ጥንቈላ፥ በእስራኤልም ላይ ምንም ዐይነት አስማት አይሠራም፤ እነሆ፥ አሁን ለያዕቆብና ለእስራኤል፥ ‘እግዚአብሔር ምን እንዳደረገ ተመልከቱ!’ ይባላል።
በለዓምም እንዲህ ሲል ትንቢት ተናገረ፦ “የሞአብ ንጉሥ ባላቅ የምሥራቅ ተራራዎች ከሚገኙበት ከሶርያ ጠርቶ አመጣኝ። እርሱም ‘ና፤ የእስራኤልን ሕዝብ አውግዝልኝ፤ እንዲጠፉም ርገምልኝ’ አለኝ።