በለዓምም “እዚሁ ዕደሩና ነገ ጧት እግዚአብሔር የሚነግረኝን ሁሉ እነግራችኋለሁ” አላቸው፤ በዚህ ዐይነት የሞአባውያን መሪዎች ከበለዓም ጋር ቈዩ።
ዘኍል 23:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በለዓምም ባላቅን “አንተ እዚህ በሚቃጠለው መሥዋዕትህ አጠገብ ቁም፤ እኔ ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት ወደዚያ እሄዳለሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በለዓምም ባላቅን፣ “እርሱን ለመገናኘት ወደዚያ ስሄድ፣ አንተ እዚሁ መሥዋዕትህ አጠገብ ቈይ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በለዓምም ባላቅን እንዲህ አለው፦ “እኔ ወደዚያ ጌታን ለማግኘት ስሄድ በዚህ በሚቃጠለው መሥዋዕትህ ዘንድ ቆይ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በለዓምም ባላቅን አለው፥ “በዚህ በመሥዋዕትህ ዘንድ ቈይ፤ እኔም እግዚአብሔርን እጠይቅ ዘንድ እሄዳለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባላቅንም፦ እኔ ወደዚያ ለመገናኘት ስሄድ በዚህ በመሥዋዕትህ ዘንድ ቆይ አለው። |
በለዓምም “እዚሁ ዕደሩና ነገ ጧት እግዚአብሔር የሚነግረኝን ሁሉ እነግራችኋለሁ” አላቸው፤ በዚህ ዐይነት የሞአባውያን መሪዎች ከበለዓም ጋር ቈዩ።
ከዚያም በፒስጋ ተራራ ጫፍ ላይ ወደሚገኘው ወደ ጾፊም መስክ ወሰደው፤ እዚያም ሰባት መሠዊያዎችን ሠርቶ በእያንዳንዱ ላይ አንድ ኰርማና አንድ አውራ በግ ሠዋ።
ከዚህ በኋላ በለዓም ባላቅን “እግዚአብሔር ወደ እኔ መምጣቱን ወይም አለመምጣቱን ለማወቅ ወደዚያ ሄጄ እስክረዳ ድረስ እዚህ በሚቃጠል መሥዋዕትህ አጠገብ ቁም፤ እግዚአብሔር የሚገልጥልኝን ነገር ሁሉ እነግርሃለሁ” አለው፤ ከዚያም በኋላ ብቻውን ወደ አንድ ኮረብታ ወጣ።