ይህም ትእዛዝ የተሰጠበት ምክንያት እስራኤላውያን ከግብጽ ምድር በወጡበት ጊዜ በጒዞ ላይ ሳሉ ሞአባውያንና ዐሞናውያን ምግብና ውሃ ስለ ከለከሉአቸው ነበር፤ ይልቁንም ይህን በማድረግ ፈንታ ለበለዓም ገንዘብ ሰጥተው የእስራኤልን ሕዝብ እንዲረግምላቸው አድርገው ነበር፤ እግዚአብሔር ግን መርገሙን ወደ በረከት ለወጠው።
ዘኍል 23:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባላቅም በለዓምን “ይህ ያደረግህብኝ ምንድን ነው? እኔ ወደዚህ ያመጣሁህ ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ነበር፤ አንተ ግን እነርሱን ከመመረቅ በቀር ምንም አላደረግህም” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባላቅም በለዓምን፣ “እንዴት እንዲህ ታደርገኛለህ? ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ አመጣሁህ፤ አንተ ግን ባረክሃቸው እንጂ ምንም አላደረግህልኝም!” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባላቅም በለዓምን እንዲህ አለው፦ “ያደረግህብኝ ምንድነው? ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ጠራሁህ፤ እነሆም፥ ፈጽመህ ባረክሃቸው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባላቅም በለዓምን፥ “ያደረግኽብኝ ምንድን ነው? ጠላቶችን ትረግምልኝ ዘንድ ጠራሁህ፤ እነሆም፥ መባረክን ባረክሃቸው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባላቅም በለዓምን፦ ያደረግህብኝ ምንድር ነው? ጠላቶቼን ትረግምልኝ ዘንድ ጠራሁህ፤ እነሆም፥ ፈጽመህ ባረክሃቸው አለው። |
ይህም ትእዛዝ የተሰጠበት ምክንያት እስራኤላውያን ከግብጽ ምድር በወጡበት ጊዜ በጒዞ ላይ ሳሉ ሞአባውያንና ዐሞናውያን ምግብና ውሃ ስለ ከለከሉአቸው ነበር፤ ይልቁንም ይህን በማድረግ ፈንታ ለበለዓም ገንዘብ ሰጥተው የእስራኤልን ሕዝብ እንዲረግምላቸው አድርገው ነበር፤ እግዚአብሔር ግን መርገሙን ወደ በረከት ለወጠው።
ባላቅ በቊጣ እጆቹን ጨብጦ በለዓምን እንዲህ አለው፤ “እኔ ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ጠርቼህ ነበር፤ አንተ ግን ስትመርቃቸው ይኸው ሦስተኛ ጊዜህ ነው።