ምን ያኽል ሀብታም እንደ ሆነና ምን ያኽል ልጆች እንዳሉት፥ ንጉሡም ሥልጣኑን ከፍ በማድረግና በመሾም የቱን ያኽል እንዳከበረው፥ ከሌሎቹ የመንግሥት ባለሥልጣኖች ይበልጥ የተከበረ ሰው መሆኑንም በትምክሕት ገለጠላቸው፤
ዘኍል 22:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከፍ ባለ ክብር አከብርሃለሁ፤ የጠየቅከኝንም ሁሉ አደርግልሃለሁ፤ ስለዚህ እባክህ መጥተህ ይህን ሕዝብ ርገምልኝ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወሮታህን በእጅጉ እከፍላለሁ፤ የምትለውንም ሁሉ አደርጋለሁ፤ ስለዚህ መጥተህ ይህን ሕዝብ ርገምልኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክብርህን እጅግ ታላቅ አደርገዋለሁና፥ የምትነግረኝንም ሁሉ አደርግልሃለሁና፥ እባክህ፥ ና፥ ይህን ሕዝብ ርገምልኝ።’ ” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክብርህን እጅግ ታላቅ አደርገዋለሁና፥ የተናገርኸውንም ሁሉ አደርግልሃለሁና ና፥ ይህን ሕዝብ ርገምልኝ ብሏል” አሉት። |
ምን ያኽል ሀብታም እንደ ሆነና ምን ያኽል ልጆች እንዳሉት፥ ንጉሡም ሥልጣኑን ከፍ በማድረግና በመሾም የቱን ያኽል እንዳከበረው፥ ከሌሎቹ የመንግሥት ባለሥልጣኖች ይበልጥ የተከበረ ሰው መሆኑንም በትምክሕት ገለጠላቸው፤
ከእነርሱም አንዱ ሐርቦና የተባለው ጃንደረባ “ንጉሥ ሆይ! ሃማን እኮ ከዚህ ሁሉ አልፎ አንተን ከሞት ያዳነህን መርዶክዮስን በስቅላት ሞት ለመቅጣት አስቦ የተከለው እንጨት በቤቱ ይገኛል፤ የእንጨቱም ርዝመት ኻያ ሁለት ሜትር ነው!” ሲል ተናገረ። ንጉሡም “ሃማንን ወስዳችሁ በዚያ እንጨት ላይ ስቀሉት!” ሲል ትእዛዝ ሰጠ።
የሕዝቡም ቊጥር ከእኛ እጅግ የበዛ ነው፤ ስለዚህ ወደዚህ መጥተህ እነርሱን ርገምልኝ፤ በዚህ ዐይነት ምናልባት ድል ልነሣቸውና ከምድሪቱ ላስወጣቸው እችል ይሆናል፤ አንተ የምትመርቀው የተመረቀ፥ አንተም የምትረግመው የተረገመ እንደሚሆን ዐውቃለሁ።”
እንግዲህስ በቶሎ ወደ ቤትህ ሂድ! እኔ በርግጥ ብዙ ዋጋ ልከፍልህ ቃል ገብቼልህ ነበር፤ ነገር ግን ይህን ዋጋ እንዳታገኝ እግዚአብሔር ዘግቶብሃል።”