አንገትሽ በዝሆን ጥርስ እንዳጌጠ ግንብ ነው፤ ዐይኖችሽ በታላቅዋ ከተማ በሐሴቦን የቅጽር በር አጠገብ የሚገኙ የውሃ ኲሬዎችን ይመስላሉ። አፍንጫሽ ወደ ደማስቆ አቅጣጫ ለመመልከት የተሠራውን የሊባኖስ ግንብ ይመስላል።
ዘኍል 21:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሐሴቦን የአሞራውያን ንጉሥ ሲሖን መናገሻ ከተማ ነበረች፤ እርሱም ከሞአብ የቀድሞ ንጉሥ ጋር ተዋግቶ እስከ አርኖን ወንዝ ያለውን ምድር ሁሉ ወስዶበት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐሴቦን የቀድሞውን የሞዓብን ንጉሥ ወግቶ እስከ አርኖን ድረስ ያለውን ምድሩን የወሰደበት የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን ከተማ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐሴቦንም የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን ከተማ ነበረ፤ እርሱም የፊተኛውን የሞዓብን ንጉሥ ወግቶ እስከ አርኖን ድረስ ምድሩን ሁሉ ከእጁ ወስዶ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐሴቦንም የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን ከተማ ነበረ፤ እርሱም የፊተኛውን የሞዓብን ንጉሥ ወግቶ ከአሮኤር እስከ አርኖን ድረስ ምድሩን ሁሉ ወስዶ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሐሴቦንም የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን ከተማ ነበረ፤ እርሱም የፊተኛውን የሞዓብን ንጉሥ ወግቶ እስከ አርኖን ድረስ ምድሩን ሁሉ ከእጁ ወስዶ ነበር። |
አንገትሽ በዝሆን ጥርስ እንዳጌጠ ግንብ ነው፤ ዐይኖችሽ በታላቅዋ ከተማ በሐሴቦን የቅጽር በር አጠገብ የሚገኙ የውሃ ኲሬዎችን ይመስላሉ። አፍንጫሽ ወደ ደማስቆ አቅጣጫ ለመመልከት የተሠራውን የሊባኖስ ግንብ ይመስላል።
የሞአብ ክብር ያልፋል፤ ሰዎች ሐሴቦንን ለመጣል ያሤራሉ፤ ‘ኑ ከእንግዲህ በሕዝብነት እንዳትታወቅ እናጥፋት’ ይላሉ፤ እናንተም የማድሜን ሰዎች ሆይ! ሰይፍ ስለሚያሳድዳችሁ ጸጥ እንድትሉ ትደረጋላችሁ።
በሽሽት የደከሙ ስደተኞች በሐሴቦን ጥላ ሥር ተጠልለዋል፤ ይህም የሆነው እሳት ከሐሴቦን፥ ነበልባልም ከሲሆን ቤቶች ወጥቶ የሞአብን ግንባር ቀደም ሠራዊትና ደጋፊ መሪዎችዋን አቃጥሎአል።
ይህም የሆነው በሐሴቦን ከተማ ነግሦ ይገዛ የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሲሖንንና በዐስታሮትና በኤድረዒ ከተሞች ሆኖ ይገዛ የነበረውን የባሳንን ንጉሥ ዖግን ድል ካደረገ በኋላ ነው።
ግዛታቸውም በአርኖን ሸለቆ ዳርቻ እስከሚገኘው እስከ ዓሮዔርና በዚያም ሸለቆ መካከል እስካለችው ከተማ አልፎ በሜደባ ዙሪያ ያለውን ሜዳማ አገር ሁሉ ያጠቃልላል፤
የእነርሱም ግዛት ያዕዜርንና በገለዓድ የሚገኙትን ከተሞች ሁሉ የዐሞንን ምድር እኩሌታ ጨምሮ ከራባ በስተምሥራቅ እስከምትገኘው እስከ ዓሮዔር ይደርሳል።
ስለዚህ ሦስት መቶ ዓመት ሙሉ እስራኤል ሐሴቦንና መንደሮችዋን ዓሮዔርንና መንደሮችዋን፥ እንዲሁም በአርኖን ወንዝ ዳርቻ ያሉትን ከተሞች በሙሉ ወርሰው ኖረዋል፤ ታዲያ በነዚህ ዘመናት ሁሉ ስለምን መልሳችሁ አልወሰዳችኋቸውም ነበር?