ዘኍል 21:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ እስራኤላውያን ይህን መዝሙር ዘመሩ “ጒድጓድ ሆይ፥ ውሃ አፍልቅ፤ ለእርሱም ዘምሩለት አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እስራኤል ይህን መዝሙር ዘመረ፤ “አንተ ምንጭ ሆይ ፍለቅ! እናንተም ዘምሩለት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ጊዜ እስራኤል ይህን መዝሙር ዘመረ፦ አንተ ምንጭ ሆይ! ፍለቅ፤ እናንተም ዘምሩለት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ጊዜ እስራኤል በዚያ ጕድጓድ አጠገብ ይህን መዝሙር ስለ ጕድጓዱ መዘመር ጀመሩ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ጊዜ እስራኤል ይህን መዝሙር ዘመረ፦ አንተ ምንጭ ሆይ፥ ፍለቅ፤ እናንተም ዘምሩለት፤ |
የውሃ ጒድጓዱን የቈፈሩት፥ መሳፍንትና የሕዝብ አለቆች ናቸው፤ እነርሱም የውሃ ጒድጓዱን የቈፈሩት በበትረ መንግሥታቸውና በከዘራቸው ነው።” ከዚያም ምድረ በዳ ተነሥተው ወደ ማታና ተጓዙ፤