የእርሱም ክፍል የሰው ብዛት ሰባ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበር።
የሰራዊቱም ብዛት ሰባ አራት ሺሕ ስድስት መቶ ነው።
ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ ሰባ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ።
የተቈጠሩ ሠራዊቱም ሰባ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ።
ፀሐይ በሚወጣበት በስተምሥራቅ በኩል የሚሰፍሩት በይሁዳ ሥር የተመደቡት ነገዶች ናቸው። የይሁዳ ነገድ መሪም የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነው።
በእርሱም አጠገብ የሚሰፍሩት የይሳኮር ነገድ ይሆናሉ፤ የይሳኮር መሪም የጾዓር ልጅ ናትናኤል ነበር፤
ከይሁዳ ነገድ የጐሣ መሪዎች የተቈጠሩት ሰባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ።