ዘኍል 2:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በስተ ሰሜን በኩል በዳን ክፍል ዓርማ ሥር የሚሰፍሩ ወገኖች ናቸው፤ የዳን ነገድ መሪ የዓሚሻዳይ ልጅ አሒዔዜር ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰሜን በኩል፤ የዳን ምድብ ሰራዊት በዐርማው ሥር ይሆናል፤ የዳን ሕዝብ አለቃ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ሲሆን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በሰሜን በኩል እንደ ሠራዊቶቻቸው የዳን ሰፈር ዓላማ ይሆናል፤ የዳንም ልጆች አለቃ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በመስዕ በኩል እንደ ሠራዊቶቻቸው የዳን ሰፈር ዓላማ ይሆናል፤ የዳንም ልጆች አለቃ የአሚሳዲ ልጅ አክያዜር ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰሜን በኩል እንደ ሠራዊቶቻቸው የዳን ሰፈር ዓላማ ይሆናል፤ የዳንም ልጆች አለቃ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ነበረ። |
የዳን ልጆች፥ በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸውና በየአባቶቻቸው ቤቶች እንደየስማቸው ቊጥር ኻያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ተቈጠሩ፤
በመጨረሻም በዳን ነገድ ቡድን ሰንደቅ ዓላማ ሥር የሚገኙትና ለሁሉም ክፍሎች ደጀን የሚሆኑት በዓሚሻዳይ ልጅ በአሒዔዜር መሪነት የቡድን ተራቸውን ጠብቀው ተጓዙ።