ዘኍል 19:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ርኲሰቱንም ለማስወገድ፥ ለኃጢአት ማስተስረያ ከተቃጠለችው ጊደር ዐመድ ጥቂት ተወስዶ በማሰሮ ውስጥ ይከተት፤ ንጹሕ የምንጭ ውሃም ይጨመርበት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለረከሰውም ሰው፣ ለማንጻት ከተቃጠለው የጊደር ዐመድ ላይ ማሰሮ ውስጥ በማድረግ በላዩ የምንጭ ውሃ ይጨምሩበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከኃጢአት ለማንጻት እንድትሆን ከተቃጠለችው ጊደር አመድ ለረከሰው ሰው ይወስዱለታል፥ በዕቃውም ውስጥ የምንጭ ውኃ ይጨመርበታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአንጽሖ እንድትሆን ከተቃጠለችው ጊደር አመድ ለርኩሱ ይወስዱለታል፤ በዕቃውም ውስጥ የምንጭ ውኃ ይቀላቅሉበታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከኃጢአት ለማንጻት እንድትሆን ከተቃጠለችው ጊደር አመድ ለርኩሱ ይወስዱለታል፥ በዕቃውም ውስጥ የምንጭ ውኃ ይቀላቀልበታል። |
አንቺ የአትክልት ቦታን እንደምታጠጣ ምንጭ ነሽ፤ የሕይወት ውሃም እንደሚገኝባት ጒድጓድ ነሽ፤ ከሊባኖስ ተራራ ሥር እንደሚፈልቅ ወንዝ ነሽ።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “በዚያን ጊዜ ለዳዊት ልጆችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ከኃጢአታቸውና ከርኲሰታቸው የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።
ቀጥሎም ንጹሕ የሆነ ሰው የሂሶጵ ቅርንጫፍ ወስዶ በውሃው ውስጥ እየነከረ በድንኳኑና በውስጡ በሚገኙት ዕቃዎች ሁሉ ላይ እንዲሁም በድንኳኑ ውስጥ በሚገኙ ሰዎች ላይ ይርጨው፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ የሆነ ሰው ዐፅም ወይም ሬሳ ወይም መቃብር በነካው ሰው ላይ ውሃ ይርጭበት፤
ከዚህ በኋላ ንጹሕ የሆነ ሌላ ሰው የጊደርዋን ዐመድ ሰብስቦ በመውሰድ ከሰፈሩ ውጪ ንጹሕ በሆነ ቦታ ያስቀምጠዋል፤ እዚያም ለእስራኤላውያን ጉባኤ ርኲሰትን ለማንጻት የሚያገለግለውን ውሃ ለማዘጋጀት የሚጠቅም ይሆናል፤ ይህም ሥርዓት የሚፈጸመው ኃጢአትን ለማስወገድ ነው።