“አንድ ሰው የራሱን ሰውም ሆነ እንስሳን ወይም መሬትን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለየ እንዲሆን ካደረገው በኋላ ፈጽሞ ሊሸጠውም ሆነ መልሶ ሊዋጀው አይገባውም።
ዘኍል 16:37 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የአሮን ልጅ አልዓዛር ከነሐስ የተሠሩትን ጥናዎች ከተቃጠሉት ሰዎች ዘንድ እንዲወስድና ጥናዎቹ የተቀደሱ ስለ ሆኑ በውስጣቸው ያለውን ፍም ወደ ሌላ ስፍራ እንዲያፈስ ንገረው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጥናዎቹ የተቀደሱ ናቸውና ከተቃጠሉት ሰዎች ዘንድ ወስደህ በውስጣቸው ያለውን ፍም አርቆ እንዲደፋ ለካህኑ ለአሮን ልጅ ለአልዓዛር ንገረው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለካህኑ ለአሮን ልጅ ለአልዓዛር እንዲህ ብለህ ተናገር፦ የተቀደሱ ናቸውና ጥናዎቹን ከሚነድደው እሳት መከካከል ውሰድ፥ እሳቱንም ወደ ውጭ አርቀህ በትነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለካህኑ ለአሮን ልጅ ለአልዓዛር እንዲህ ብለህ ንገረው፥ “ከተቃጠሉት ሰዎች መካከል የናስ የሚሆኑ ጥናዎችን አውጣ፤ ከሌላ ያመጡትን ያንም እሳት ወዲያ ጣል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለካህኑ ለአሮን ልጅ ለአልዓዛር እንዲህ ብለህ ንገረው፦ ተቀድሰዋልና ጥናዎቹን ከተቃጠሉት ዘንድ ውሰድ፥ እሳቱንም ወደ ውጭ ጣለው፤ |
“አንድ ሰው የራሱን ሰውም ሆነ እንስሳን ወይም መሬትን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለየ እንዲሆን ካደረገው በኋላ ፈጽሞ ሊሸጠውም ሆነ መልሶ ሊዋጀው አይገባውም።
ጥናዎቹም የተቀደሱት ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ በቀረቡ ጊዜ ነው፤ ስለዚህ በኃጢአታቸው የተገደሉትን የእነዚህን ሰዎች ጥናዎች ውሰድና በመቀጥቀጥ እንዲሳሱ አድርግ፤ ለመሠዊያውም መክደኛ እንዲሆኑ አድርገህ ሥራቸው፤ ለእስራኤል ሕዝብ የመቀጣጫ ማስጠንቀቂያ ይሆናል።”
በእነርሱም ላይ የከሰል ፍምና ዕጣን አድርጋችሁ ወደ መሠዊያው አቅርቡአቸው፤ ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ማንኛችንን መርጦ ለራሱ እንደ ለየ እናያለን፤ ከልክ ያለፋችሁትስ እናንተ ሌዋውያኑ ናችሁ።”