“ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ይህ ነው፦ ማንም ሰው ተሳስቶ ኃጢአት ቢሠራ ወይም ባለማወቅ ከእግዚአብሔር ትእዛዞች አንዱን ቢተላለፍ ከዚህ የሚከተለውን ሥርዓት ይጠብቅ፦
ዘኍል 15:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው በግሉ ባለማወቅ ኃጢአት ቢሠራ አንድ ዓመት የሞላት እንስት ፍየል ስለ ኃጢአቱ ስርየት መሥዋዕት አድርጎ ያቅርብ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ነገር ግን አንድ ሰው ካለማወቅ የተነሣ በግሉ ኀጢአት ቢሠራ ግን ለኀጢአት መሥዋዕት የአንድ ዓመት እንስት ፍየል ያምጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አንድ ሰው ባለማወቅ ኃጢአት ቢሠራ፥ ለኃጢአት መሥዋዕት አንዲት የአንድ ዓመት እንስት ፍየል ያቀርባል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አንድ ሰው ሳያውቅ ኀጢአት ቢሠራ፥ ስለ ኀጢአት አንዲት የአንድ ዓመት እንስት ፍየል ያቀርባል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንድ ሰው ሳያውቅ ኃጢአት ቢሠራ፥ ለኃጢአት መሥዋዕት አንዲት የአንድ ዓመት እንስት ፍየል ያቀርባል። |
“ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ይህ ነው፦ ማንም ሰው ተሳስቶ ኃጢአት ቢሠራ ወይም ባለማወቅ ከእግዚአብሔር ትእዛዞች አንዱን ቢተላለፍ ከዚህ የሚከተለውን ሥርዓት ይጠብቅ፦
እዚያ ቊርባኑን ለእግዚአብሔር ያቀርባል፤ ይኸውም ለሚቃጠል መሥዋዕት አንድ ዓመት የሞላው የበግ ጠቦት፥ ስለ ኃጢአት ስርየት ለሚቀርበውም መሥዋዕት አንድ ዓመት የሞላት አንዲት የበግ ቄብ እንዲሁም የአንድነት መሥዋዕት አንድ አውራ በግ ያቀርባል ማለት ነው።
ነገር ግን የጌታውን ፈቃድ ባለማወቅ፥ ቅጣት የሚያመጣበትን ነገር አድርጎ ቢገኝ ቅጣቱ ይቀልለታል፤ ብዙ ከተሰጠው ሰው ብዙ ይፈለግበታል፤ ብዙ ዐደራም ከተሰጠው ሰው፥ ብዙ ይጠበቅበታል።”
እንግዲህ ሰዎች በቀድሞ ዘመን ባለማወቅ ያደረጉትን እግዚአብሔር ችላ ብሎ አልፎታል፤ አሁን ግን በየአገሩ ያሉ ሰዎች ሁሉ ንስሓ እንዲገቡ አዞአል፤
ምንም እንኳ ከዚህ ቀደም ክርስቶስን የሰደብኩና ያሳደድኩ፥ ያዋረድኩም ብሆን፤ እርሱ ምሕረት አደረገልኝ፤ እርሱም ይህን ምሕረት ያደረገልኝ እኔ ይህን ሁሉ ያደረግኹት ባለማወቅና ባለማመን ስለ ነበረ ነው።