ከዚህም በኋላ በጋት ላይ ጦርነት ተደረገ፤ በዚያም ጦርነት የሚወድ አንድ ኀያል ሰው ነበረ፤ ያም ኀያል ሰው በእጆቹና በእግሮቹ ስድስት ስድስት ጣቶች ነበሩት፤ እርሱም ከራፋይም የተወለደ ነበር።
ዘኍል 13:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሊሰልሉ ስለ ሄዱበት አገርም ለእስራኤላውያን ያቀረቡት ዘገባ ተስፋ አስቈራጭ ነበር፥ እነርሱም፥ “ልንሰልል የሄድንበት አገር ወደ እርስዋ ለመኖር የሚመጣውን ሰው የምትውጥ ናት፤ እዚያ ያየናቸው ሰዎች ረጃጅሞች ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህም ስለ ሰለሏት ምድር በእስራኤላውያን መካከል እንዲህ የሚል መጥፎ ወሬ አሠራጩ፤ “ያየናት ምድር የሚኖሩባትን ሰዎች የምትበላ ናት፤ እዚያ ያየናቸው ሰዎች ሁሉ ግዙፎች ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ሰለሉአትም ምድር ክፉ ወሬ ለእስራኤል ልጆች አወሩ እንዲህም አሉ፦ “እኛ ዞረን የሰለልናት ምድር የሚኖሩባትን ሰዎች የምትበላ ምድር ናት፤ በእርሷም ዘንድ ያየናቸው ሰዎች ሁሉ ረጃጅም ሰዎች ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ሰለሉአትም ምድር ለእስራኤል ልጆች እያወሩ፥ “እኛ ዞረን የሰለልናት ምድር የሚኖሩባትን ሰዎች የምትበላ ምድር ናት፤ በእርስዋም ዘንድ ያየናቸው ሰዎች ሁሉ ረጃጅም ሰዎች ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ሰለሉአትም ምድር ክፉ ወሬ ለእስራኤል ልጆች እያወሩ፦ እኛ ዞረን የሰለልናት ምድር የሚኖሩባትን ሰዎች የምትበላ ምድር ናት፤ በእርስዋም ዘንድ ያየናቸው ሰዎች ሁሉ ረጃጅም ሰዎች ናቸው። |
ከዚህም በኋላ በጋት ላይ ጦርነት ተደረገ፤ በዚያም ጦርነት የሚወድ አንድ ኀያል ሰው ነበረ፤ ያም ኀያል ሰው በእጆቹና በእግሮቹ ስድስት ስድስት ጣቶች ነበሩት፤ እርሱም ከራፋይም የተወለደ ነበር።
ሌላም ጦርነት በጋት ተደረገ፤ በዚያም ጦርነት በእያንዳንዱ እጅና በእያንዳንዱ እግር ላይ ስድስት ስድስት በጠቅላላ ኻያ አራት ጣቶች የነበሩት አንድ ረጅም ሰው ነበር፤ እርሱም ኀያላን ከሆኑት ከራፋይም ዘር ነበር፤
ሕዝቤ እስራኤል ሆይ! እንደገና በምድሪቱ መኖር ትችሉ ዘንድ መልሼ አመጣችኋለሁ፤ ምድሪቱም እንደገና ተመልሳ የራሳችሁ ትሆናለች፤ ዳግመኛም ልጆች አልባ አትሆንም።
“እኔ ግን ለእናንተ ስል ቁመታቸው እንደ ሊባኖስ ዛፍ፥ ብርታታቸው እንደ ዋርካ ዛፍ የነበረውን አሞራውያንን ከነሥር መሠረታቸው ነቃቅዬ አጠፋሁላችሁ፤
ነገር ግን በዚያች ምድር የሚኖሩ ሕዝብ እጅግ ብርቱዎች ናቸው፤ ከተሞቻቸውም ታላላቆችና የተመሸጉ ናቸው፤ ከዚህም ሁሉ በላይ እጅግ ግዙፋን የዐናቅ ዘሮች አይተናል።
“ሰው ወደ መንግሥተ ሰማይ እንዳይገባ፥ በሩን የምትዘጉ እናንተ ግብዞች፥ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን! ወዮላችሁ! እናንተ ራሳችሁ አትገቡበትም፤ መግባት የሚፈልጉትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ!” [
ታዲያ እዚያ የምንሄደው ለምንድን ነው? እንፈራለን፤ የላክናቸውም ሰዎች በዚያ የሚኖሩት ሁሉ ብርቱዎችና በቁመታቸውም ከእኛ ይበልጥ ረጃጅሞች መሆናቸውን፥ እንዲሁም ርዝመታቸው እስከ ሰማይ የሚደርስ የግንብ ቅጽሮች ባሉአቸው ከተሞች የሚኖሩ መሆናቸውን ነገሩን፤ እጅግ ግዙፋን የሆኑ የዔናቅ ልጆችንም አይተዋል።’