አገልጋዩ ግን “ይህ ለመቶ ሰው የሚበቃ ይመስልሃልን?” ሲል ጠየቀው። ኤልሳዕም “እንዲበሉ አቅርብላቸው፤ በልተው መጥገብ ብቻ ሳይሆን እንደሚተርፋቸውም እግዚአብሔር ተናግሮአል” አለው።
ዘኍል 11:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምንበላውን ሥጋ ስጠን እያሉ ወደ እኔ መጥተው ስለሚያለቅሱ ለእነዚህ ሰዎች ሁሉ የሚሆን ሥጋ ከወዴት አመጣለሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለዚህ ሁሉ ሕዝብስ ሥጋ ከወዴት አመጣለሁ? ሁሉም ‘የምንበላው ሥጋ ስጠን’ እያሉ ያለቅሱብኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም በፊቴ እያለቀሱ እንዲህ ይላሉና፦ ‘የምንበላውን ሥጋ ስጠን’፤ እንግዲህ ለዚህ ሕዝብ ሁሉ የምሰጠው ሥጋ ከወዴት አገኛለሁ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፊቴ ያለቅሳሉና፦ የምንበላውን ሥጋ ስጠን ይላሉና ለዚህ ሕዝብ ሁሉ የምሰጠው ሥጋ ከየት አለኝ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፊቴ ያለቅሳሉና፦ የምንበላውን ሥጋ ስጠን ይላሉና ለዚህ ሕዝብ ሁሉ የምሰጠው ሥጋ ከወዴት እወስዳለሁ? |
አገልጋዩ ግን “ይህ ለመቶ ሰው የሚበቃ ይመስልሃልን?” ሲል ጠየቀው። ኤልሳዕም “እንዲበሉ አቅርብላቸው፤ በልተው መጥገብ ብቻ ሳይሆን እንደሚተርፋቸውም እግዚአብሔር ተናግሮአል” አለው።
በዚህ ጊዜ የንጉሡ የቅርብ ባለሟል የሆነ አገልጋዩ ኤልሳዕን፥ “እግዚአብሔር ራሱ የሰማይ መስኮቶችን ከፍቶ እህልን እንደ ዝናብ ቢያዘንብ እንኳ ይህ ሊሆን ከቶ አይችልም!” ሲል በመጠራጠር ተናገረ። ኤልሳዕም “ያን እህል በዐይንህ ታያለህ፤ ነገር ግን ከእርሱ ምንም ነገር አትቀምስም!” አለው።
እስኪያንገፈግፋችሁና በአፍንጫችሁ እስኪወጣ ድረስ አንድ ወር ሙሉ ትመገቡታላችሁ፤ ይህም የሚሆነው እዚህ በመካከላችሁ ያለውን ጌታ ስለ ናቃችሁና፦ ከግብጽ ባልወጣን ኖሮ መልካም ነበር በማለት ስላለቀሳችሁ ነው።’ ”
ሙሴም ለእግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ እኔ ስድስት መቶ ሺህ ሕዝብ በመምራት ላይ እገኛለሁ፤ ለአንድ ወር የሚበቃ ሥጋ ልትሰጣቸው ቃል ገብተሃል፤
ታዲያ ምን ያኽል የከብትና የበግ መንጋ ቢታረድ እነርሱን ሊያጠግብ ይችላል? በባሕር ውስጥ ያለው ዓሣ ሁሉ ቢሰበሰብ ለእነርሱ በቂ ሊሆን ይችላልን?”