አባቱ ግን “ዐውቄአለሁ፤ ልጄ ዐውቄአለሁ፤ የምናሴም ዘር ታላቅ ሕዝብ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ የእርሱ ታናሽ ወንድም ከእርሱ ይበልጥ ታላቅ ይሆናል፤ ዘሮቹም ታላላቅ ሕዝቦች ይሆናሉ” አለ።
ዘኍል 10:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም በኤፍሬም ነገድ ክፍል ዓርማ ሥር የሚገኙት በዓሚሁድ ልጅ በኤሊሻማዕ መሪነት የቡድን ተራቸውን ጠብቀው ተጓዙ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀጥሎም የኤፍሬም ሰፈር ሰራዊት በዐርማቸው ሥር ሆነው ተጓዙ፤ አለቃቸውም የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኤፍሬምም ልጆች ሰፈር ዓላማ በየሠራዊታቸው ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ አለቃ ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኤፍሬምም ልጆች ሰፈር በሥርዐታቸው ከየሠራዊቶቻቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የኣሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ አለቃ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኤፍሬምም ልጆች ሰፈር ዓላማ በየሠራዊታቸው ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ አለቃ ነበረ። |
አባቱ ግን “ዐውቄአለሁ፤ ልጄ ዐውቄአለሁ፤ የምናሴም ዘር ታላቅ ሕዝብ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ የእርሱ ታናሽ ወንድም ከእርሱ ይበልጥ ታላቅ ይሆናል፤ ዘሮቹም ታላላቅ ሕዝቦች ይሆናሉ” አለ።