La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ነህምያ 7:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከምርኮኞች ብዙዎቹ ከባቢሎን አውራጃዎች ተነሥተው፥ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ምድር በመመለስ፥ እያንዳንዱ ወደ ገዛ ከተማው ገብቶአል፤ ናቡከደነፆር ከወሰዳቸው ጊዜ ጀምሮ ቤተሰቦቻቸው በባቢሎን ምድር ይኖሩ ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ማርኮ ከወሰዳቸው ምርኮኞች መካከል የተመለሱት የአውራጃው ተወላጆች እነዚህ ናቸው፤ እያንዳንዳቸውም በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ወደሚገኙት ወደ የራሳቸው ከተሞች ተመለሱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ ገዛ ከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ከማ​ረ​ካ​ቸው ምር​ኮ​ኞች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና ወደ ይሁዳ፥ ወደ እየ​ከ​ተ​ማ​ቸው የተ​መ​ለ​ሱት የሀ​ገር ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው።

Ver Capítulo



ነህምያ 7:6
10 Referencias Cruzadas  

ከዚህም በኋላ ናቡዛርዳን በከተማይቱ ቀርተው የነበሩትንና ሌሎችን ሰዎች፥ እንዲሁም ከድተው ወደ ባቢሎናውያን የተጠጉትን ሁሉ ይዞ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤


ወደ ይሁዳ ምድር ሄደን የታላቁ አምላክ ቤተ መቅደስ በድንጋይና በጠርብ እንጨት ሲሠራ ማየታችን ለግርማዊነትዎ የታወቀ ይሁን፤ ሥራውም በሽማግሌዎቹ መሪነት በጥንቃቄና በፍጥነት እየተሠራ ነው።


ነገር ግን በባቢሎን ከተማ ሳይሆን በሜዶን ክፍለ ሀገር በተለይ “አሕምታ” ተብላ በምትጠራው ከተማ ውስጥ አንድ የብራና ጥቅል ተገኘ፤ በውስጡም የተጻፈበት ቃል እንዲህ የሚል ነበር፦


እነርሱም “ተማርከው ወደ ባቢሎን ሳይወሰዱ የቀሩትና በሕይወት ያሉት አይሁድ በታላቅ ችግርና ኀፍረት ላይ ወድቀው ይገኛሉ፤ የኢየሩሳሌምም ቅጽሮች ፈራርሰው ወድቀዋል፤ የቅጽር በሮቹም በእሳት ጋይተዋል” ሲሉ መለሱልኝ።


ሲመለሱም መሪዎቻቸው ዘሩባቤል፥ ኢያሱ፥ ነህምያ፥ ዐዛርያ፥ ረዓምያ፥ ናሐማኒ፥ መርዶክዮስ፥ ቢልሻን፥ ሚስፔሬት፥ ቢግዋይ፥ ነሑምና በዓና ናቸው።