ነህምያ 2:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሸለቆ ቅጽር በር ወጥቼ የዘንዶ ምንጭ ተብሎ የሚጠራውን ስፍራ በማለፍ፥ በስተ ደቡብ ወደሚገኘው የጒድፍ መጣያ ተብሎ ወደሚጠራው ስፍራ ሄድኩ፤ ጊዜውም ገና ሌሊት ነበር፤ በማልፍበትም ጊዜ የፈራረሱትን የከተማይቱን ቅጽሮችና በእሳት የወደሙትን የቅጽር በሮች ጐበኘሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሌሊትም ወጥቼ በሸለቆው በር በኩል አድርጌ ወደ ዘንዶው የውሃ ጕድጓድና ወደ ቈሻሻ መድፊያው በር ሄድሁ፤ የፈረሱትንም የኢየሩሳሌምን ቅጥሮችና በእሳት የወደሙትን በሮች ተመለከትሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሌሊትም በሸለቆው በር ወጣሁ፥ ወደ “የዘንዶ ምንጭ” እና ወደ “የፍግ በር” ሄድኩ፤ የፈረሰውን የኢየሩሳሌምን ቅጥርና በእሳት የተቃጠሉትን በሮችዋን ተመለከትኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሸለቆውም በር ወጣሁ፤ ወደ በለስም ምንጭና ወደ ጕድፍ መጣያው በር ሄድሁ፤ የፈረሰውንም የኢየሩሳሌምን ቅጥር፥ በእሳትም የተቃጠሉትን በሮችዋን ተመለከትሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሸለቆውም በር ወጣሁ፤ ወደ ዘንዶውም ምንጭና ወደ ጉድፍ መጣያው በር ሄድሁ፤ የፈረሰውንም የኢየሩሳሌምን ቅጥር፥ በእሳትም የተቃጠሉትን በሮችዋን ተመለከትሁ። |
እነርሱም “ተማርከው ወደ ባቢሎን ሳይወሰዱ የቀሩትና በሕይወት ያሉት አይሁድ በታላቅ ችግርና ኀፍረት ላይ ወድቀው ይገኛሉ፤ የኢየሩሳሌምም ቅጽሮች ፈራርሰው ወድቀዋል፤ የቅጽር በሮቹም በእሳት ጋይተዋል” ሲሉ መለሱልኝ።
እኔም ነህምያ የይሁዳን መሪዎች በቅጽሩ ላይ እንዲወጡ ካደረግሁ በኋላ ሁለት ታላላቅ የመዘምራን ቡድን የምስጋና መዝሙር እንዲዘምሩ አደረግሁ፤ የመጀመሪያው ቡድን በቅጽሩ ግንብ አናት ላይ በስተቀኝ በኩል ወደሚገኘው ወደ ጒድፍ መጣያው የቅጽር በር በኩል አለፈ፤
ለኢየሩሳሌም ስለማከናውነው ሥራ ሁሉ እግዚአብሔር ለእኔ የገለጠልኝን ምሥጢር ለማንም ሳልናገር ቈየሁ፤ ከዚያም በኋላ ከጓደኞቼ ጥቂቶቹን በማስከተል፥ በእኩለ ሌሊት ተነሥቼ ሄድኩ፤ የነበረን የጭነት እንስሳ እኔ የተቀመጥኩበት ብቻ ነበር፤
ስለዚህ ሌሊቱን ወደ ቄድሮን ወንዝ በመውረድ፥ ቅጽሮችን እየጐበኘሁ አልፌ ሄድኩ፤ በመጨረሻም በዚያው በመጣሁበት መንገድ ተመልሼ በሸለቆው ቅጽር በር በኩል ወደ ከተማይቱ ገባሁ።
ከዚህ በኋላ ግን “እንግዲህ ያለውን ችግር ሁሉ ተመልከቱት! ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ሆናለች፤ የቅጽር በሮችዋም በእሳት ወድመዋል፤ ስለዚህ ተነሥተን የከተማይቱን ቅጽሮች እንሥራ፤ የደረሰብንንም ኀፍረት እናስወግድ” አልኳቸው።
“ንጉሠ ነገሥቱ ለዘለዓለም ይኑር! የቀድሞ አባቶቼ የተቀበሩባት ከተማ ፍርስራሽ ሆና ስትቀርና የቅጽሮችዋም በሮች በእሳት ሲወድሙ እንዴት አላዝንም?” ስል መለስኩለት።
የሕዝቤን የወይን ተክል ቈራርጠው የሚያበላሹ ጠላቶችን እልካለሁ፤ ነገር ግን ሥር መሠረታቸውን እንዲያጠፉ አላደርግም፤ ቅርንጫፎቹ የእኔ ባለመሆናቸው፥ ቈርጠው እንዲጥሉአቸው አዛለሁ።