በእነዚያም ቀኖች በይሁዳ በሰንበት ቀን ወይን የሚጨምቁ፥ እህልን፥ ወይን ጠጅን፥ የወይን ዘለላን፥ በለስን፥ ሌሎችንም ነገሮች ሁሉ በአህያ የሚጭኑ መሆናቸውን አየሁ፤ እነዚህንም ሁሉ በሰንበት ቀን ወደ ኢየሩሳሌም አምጥተው እንዳይሸጡ አስጠነቀቅኋቸው።
ነህምያ 13:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም ጋር በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የጢሮስ ተወላጆች ዓሣና ሌሎች ሸቀጦችን በየዐይነቱ በሰንበት ቀን ወደ ከተማይቱ እያስገቡ ለይሁዳ ሕዝብ ይሸጡ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የጢሮስ ሰዎችም ዓሣና ልዩ ልዩ ሸቀጣ ሸቀጥ በሰንበት ቀን እያመጡ ለይሁዳ ሕዝብ በኢየሩሳሌም ይሸጡ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም በእርሷ የተቀመጡ የጢሮስ ሰዎች ነበሩ፥ እነርሱም ዓሣዎችን ልዩ ልዩም ዓይነት ሸቀጥ አምጥተው በሰንበት ቀን በኢየሩሳሌም ለይሁዳ ልጆች ይሸጡ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም በእርስዋ የተቀመጡ ነበሩ፤ እነርሱም ዓሣዎችን፥ ልዩ ልዩም ዓይነት ሸቀጥ አምጥተው በሰንበት ቀን በኢየሩሳሌም ለይሁዳ ልጆች ይሸጡ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም በእርስዋ የተቀመጡ የጢሮስ ሰዎች ነበሩ፥ እነርሱም ዓሣዎችን ልዩ ልዩም ዓይነት ሸቀጥ አምጥተው በሰንበት ቀን በኢየሩሳሌም ለይሁዳ ልጆች ይሸጡ ነበር። |
በእነዚያም ቀኖች በይሁዳ በሰንበት ቀን ወይን የሚጨምቁ፥ እህልን፥ ወይን ጠጅን፥ የወይን ዘለላን፥ በለስን፥ ሌሎችንም ነገሮች ሁሉ በአህያ የሚጭኑ መሆናቸውን አየሁ፤ እነዚህንም ሁሉ በሰንበት ቀን ወደ ኢየሩሳሌም አምጥተው እንዳይሸጡ አስጠነቀቅኋቸው።
ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የዕረፍት ቀን ነው፤ በዚያን ቀን ማንም ሰው ሥራ አይሥራ፤ አንተም ሆንክ ልጆችህ፥ አገልጋዮችህም ሆኑ እንስሶችህ፥ በአገርህ ውስጥ የሚኖሩ መጻተኞችም ቢሆኑ ምንም ሥራ አትሥሩበት።
“በሳምንት ስድስት ቀን ሥራህን ሁሉ ሥራ፤ በሰባተኛው ቀን ግን ምንም ሥራ አትሥራበት፤ በዚህ ዐይነት አገልጋዮችህና ለአንተ የሚሠሩ መጻተኞች፥ እንዲሁም በሬህና አህያህ ዕረፍት አድርገው ይዋሉ።
ሰባተኛው ቀን ግን ለእኔ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የዕረፍት ቀን ነው፤ በዚያን ቀን ምንም ዐይነት ሥራ አትሥራ፤ አንተም ሆንክ ልጆችህ፥ አገልጋዮችህም ሆኑ እንስሶችህ በአገርህ ውስጥ የሚኖሩ መጻተኞችም ቢሆኑ ምንም ሥራ አትሥሩበት፤ አገልጋዮችህም ልክ እንደ አንተው ዕረፍት ያድርጉ።