ሌዋውያን፦ ሸማዕያ የሐሹብ ልጅ፥ የዓዝሪቃም ልጅ፥ የሐሻብያን ልጅ፥ የቡኒን ልጅ፥
ከሌዋውያኑ፦ የቡኒ ልጅ፣ የአሳብያ ልጅ፣ የዓዝሪቃም ልጅ፣ የአሱብ ልጅ ሸማያ፤
ከሌዋውያንም የቡኒ ልጅ፥ የሐሻብያ ልጅ፥ የዓዝሪቃም ልጅ፥ የሐሹብ ልጅ ሽማዕያ፤
ከሌዋውያንም የቡኒ ልጅ፥ የአሳብያ ልጅ፥ የዓዝሪቃም ልጅ፥ የሐሱብ ልጅ ሰማያ፤
ከሌዋውያንም የቡኒ ልጅ የአሳብ ልጅ የዓዝሪቃም ልጅ የአሱብ ልጅ ሻማያ፥
በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩት ሌዋውያን የሚከተሉት ናቸው፦ የሐሹብ ልጅ ሸማዕያ፤ የእርሱም የቀድሞ አባቶች ከመራሪ ጐሣዎች የነበሩት ዓዝሪቃምና ሐሻብያ ናቸው። ባቅባቃር፥ ሔሬሽና ጋላል፤ የሚካ ልጅ ማታንያ፤ የእርሱም የቀድሞ አባቶች ዚክሪና አሳፍ ናቸው። የሸማዕያ ልጅ አብድዩ የእርሱም የቀድሞ አባቶች ጋላልና ይዱታን ናቸው። የነጦፋ ከተማ ይዞታ በነበረው ግዛት ይኖር በነበረው የኤልቃና የልጅ ልጅ የአሳ ልጅ ቤሬክያ።
የኤቢያሳፍ የልጅ ልጅ የቆሬ ልጅ ሻሉም የቆሬ ጐሣ አባሎች ከሆኑት ከሌሎች ዘመዶቹ ጋር በመሆን የቀድሞ አባቶቻቸው የእግዚአብሔርን ሰፈር ይጠብቁ በነበረው ዐይነት እግዚአብሔር ወደሚመለክበት ድንኳን የሚያስገባውን በር ይጠብቁ ነበር።
የእርሱም ወንድሞች ስመጥር ወታደሮች የሆኑት አባላት ብዛት 128 ነበር፤ መሪያቸውም ዛብድኤል ተብሎ የሚጠራ የሐጌዶሊም ልጅ ነበር።
ሻበታይና ዮዛባድ ተብለው የሚጠሩ የሌዋውያን መሪዎች ከቤተ መቅደስ በስተውጭ ለሚሠራው ነገር ሁሉ ኀላፊዎች ነበሩ።