ስለዚህም ንጉሥ ሆይ! ይህች ከተማ እንደገና ከተሠራችና የቅጽሮችዋም ሥራ ከተጠናቀቀ፥ ሕዝቡ ግብር መክፈላቸውን ያቆማሉ፤ ለግርማዊነትዎ የሚቀርበውም የንጉሣዊ ቤተ መንግሥት ገቢ ሊቀነስ የሚችል መሆኑን ይታወቅ፤
ማቴዎስ 9:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ከዚያ ቦታ ተነሥቶ ሲሄድ ሳለ ማቴዎስ የተባለውን ቀራጭ በቀረጥ መቀበያ ስፍራ ተቀምጦ አየውና “ተከተለኝ!” አለው፤ እርሱም ተነሥቶ ተከተለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ከዚያ ተነሥቶ ሲሄድ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው በቀረጥ መሰብሰቢያው ተቀምጦ አየና፣ “ተከተለኝ” አለው፤ እርሱም ተነሥቶ ተከተለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም ከዚያ አልፎ ሲሄድ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው በቀረጥ መቀበያ ስፍራ ተቀምጦ አየውና “ተከተለኝ” አለው። ተነሥቶም ተከተለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው አየና “ተከተለኝ” አለው። ተነሥቶም ተከተለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው አየና፦ ተከተለኝ አለው። ተነሥቶም ተከተለው። |
ስለዚህም ንጉሥ ሆይ! ይህች ከተማ እንደገና ከተሠራችና የቅጽሮችዋም ሥራ ከተጠናቀቀ፥ ሕዝቡ ግብር መክፈላቸውን ያቆማሉ፤ ለግርማዊነትዎ የሚቀርበውም የንጉሣዊ ቤተ መንግሥት ገቢ ሊቀነስ የሚችል መሆኑን ይታወቅ፤
ከዚያም በኋላ ኢየሱስ በማቴዎስ ቤት በማእድ ተቀምጦ ሳለ ብዙ ቀራጮችና ኃጢአተኞች፥ ወደዚያ መጥተው ከእርሱና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በማእድ ተቀመጡ።
ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው ወደሚኖሩበት ሰገነት ላይ ወጡ፤ እነርሱም “ጴጥሮስ፥ ዮሐንስ፥ ያዕቆብ፥ እንድርያስ፥ ፊልጶስ፥ ቶማስ፥ በርተሎሜዎስ፥ ማቴዎስ፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፥ ቀናተኛው ስምዖንና የያዕቆብ ልጅ ይሁዳ” ናቸው።