በዚያን ጊዜ ኢየሱስ “አንቺ ሴት እምነትሽ! ትልቅ ነው፤ ስለዚህ እንደ ፍላጎትሽ ይሁንልሽ!” አላት። የሴትዮዋም ልጅ በዚያኑ ሰዓት ዳነች።
ማቴዎስ 9:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ዐይኖቻቸውን በእጁ ዳሰሰና፦ “እንደ እምነታችሁ ይሁንላችሁ!” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢየሱስ ዐይኖቻቸውን ዳስሶ፣ “እንደ እምነታችሁ ይሁንላችሁ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ ዐይኖቻቸውን ዳሰሰና “እንደ እምነታችሁ ይሁንላችሁ” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ጊዜ “እንደ እምነታችሁ ይሁንላችሁ፤” ብሎ ዐይኖቻቸውን ዳሰሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜ፦ እንደ እምነታችሁ ይሁንላችሁ ብሎ ዓይኖቻቸውን ዳሰሰ። |
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ “አንቺ ሴት እምነትሽ! ትልቅ ነው፤ ስለዚህ እንደ ፍላጎትሽ ይሁንልሽ!” አላት። የሴትዮዋም ልጅ በዚያኑ ሰዓት ዳነች።
ኢየሱስ ወደ ቤት በገባ ጊዜ ዕውሮቹ ወደ እርሱ ቀረቡ፤ እርሱም “እኔ ይህን ማድረግ እንደምችል ታምናላችሁን?” አላቸው። እነርሱም “አዎ፥ ጌታ ሆይ!” ሲሉ መለሱ።