ማቴዎስ 9:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ወደ ቤት በገባ ጊዜ ዕውሮቹ ወደ እርሱ ቀረቡ፤ እርሱም “እኔ ይህን ማድረግ እንደምችል ታምናላችሁን?” አላቸው። እነርሱም “አዎ፥ ጌታ ሆይ!” ሲሉ መለሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐይነ ስውሮቹም ኢየሱስ ወደ ገባበት ቤት ተከትለው ገቡ፤ ኢየሱስም፣ “ዐይናችሁን ላበራላችሁ እንደምችል ታምናላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “አዎን፣ ጌታ ሆይ፤” ብለው መለሱለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ቤት በገባ ጊዜ ዓይነ ስውሮቹ ወደ እርሱ ቀረቡ፤ ኢየሱስም “ይህን ማድረግ እንደምችል ታምናላችሁን?” አላቸው። እነርሱም “አዎን ጌታ ሆይ!” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ዕውሮቹ ወደ እርሱ ቀረቡ፤ ኢየሱስም “ይህን ማድረግ እንድችል ታምናላችሁን?” አላቸው። “አዎን፥ ጌታ ሆይ!” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ዕውሮቹ ወደ እርሱ ቀረቡ፥ ኢየሱስም፦ ይህን ማድረግ እንድችል ታምናላችሁን? አላቸው። አዎን፥ ጌታ ሆይ አሉት። |
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ሕዝቡን አሰናብቶ ወደ ቤት ገባ፤ ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው፥ “የእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ትርጒም አስረዳን” አሉት።
ይህ ሰው ጳውሎስ በሚናገርበት ጊዜ ተቀምጦ ያዳምጥ ነበር፤ ጳውሎስ ሰውየውን ትኲር ብሎ ተመለከተና ለመዳን የሚያበቃው እምነት እንዳለው ባየ ጊዜ፥