ማቴዎስ 9:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በጀልባ በመሳፈር ባሕሩን ተሻግሮ ወደ ራሱ ከተማ መጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ባሕሩን በጀልባ ተሻግሮ ወደ ራሱ ከተማ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ጀልባ ገብቶ ተሻገረና ወደ ገዛ ከተማው መጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በታንኳም ገብቶ ተሻገረና ወደ ገዛ ከተማው መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በታንኳም ገብቶ ተሻገረና ወደ ገዛ ከተማው መጣ። |
የተቀደሰውን ነገር ለውሾች አትስጡ፤ ዕንቋችሁንም በዐሣማዎች ፊት አትጣሉ፤ ዐሣማዎቹ ዕንቋችሁን በእግራቸው ይረግጡታል፤ ውሾቹም ተመልሰው ይነክሱአችኋል።
ከዚህ በኋላ የጌርጌሴኖን አካባቢ ሰዎች ሁሉ ኢየሱስ ከአገራቸው እንዲሄድላቸው ለመኑት። ይህንንም ያሉበት ምክንያት በጣም ፈርተው ስለ ነበረ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ በጀልባ ተሳፈረና ወደ መጣበት ስፍራ ተመልሶ ሄደ።