እኔ ባሪያህ ይህን ያኽል ቸርነትና ታማኝነት ልታሳየኝ የሚገባኝ አልነበርኩም፤ ዮርዳኖስን ተሻግሬ ስመጣ ከምመረኰዘው በትር በቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን እነዚህን በሁለት ቡድን የተከፈሉ ወገኖች ይዤ ተመልሻለሁ።
ማቴዎስ 8:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመቶ አለቃው ግን እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ጌታ ሆይ! አንተ ወደ ቤቴ እንድትገባ እኔ የተገባሁ ሰው አይደለሁም፤ ነገር ግን አንዲት ቃል ብቻ ተናገር፤ አገልጋዬም ይድናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመቶ አለቃው ግን መልሶ እንዲህ አለ፤ “ጌታ ሆይ፤ ወደ ቤቴ እንድትገባ የሚገባኝ አይደለሁም፤ ነገር ግን ከዚሁ ሆነህ አንዲት ቃል ብቻ ተናገር፤ ብላቴናዬም ይፈወሳል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመቶ አለቃውም እንዲህ ሲል መለሰ “ጌታ ሆይ! ከቤቴ ጣራ በታች ልትገባ አይገባኝም፤ ነገር ግን ቃል ብቻ ተናገር፤ ብላቴናዬም ይፈወሳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመቶ አለቃውም መልሶ “ጌታ ሆይ! በቤቴ ጣራ በታች ልትገባ አይገባኝም፤ ነገር ግን ቃል ብቻ ተናገር፤ ብላቴናዬም ይፈወሳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመቶ አለቃውም መልሶ፦ ጌታ ሆይ፥ በቤቴ ጣራ ከታች ልትገባ አይገባኝም፤ ነገር ግን ቃል ብቻ ተናገር፥ ብላቴናዬም ይፈወሳል። |
እኔ ባሪያህ ይህን ያኽል ቸርነትና ታማኝነት ልታሳየኝ የሚገባኝ አልነበርኩም፤ ዮርዳኖስን ተሻግሬ ስመጣ ከምመረኰዘው በትር በቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን እነዚህን በሁለት ቡድን የተከፈሉ ወገኖች ይዤ ተመልሻለሁ።
“በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ያለውን በትር ወስደህ አንተና አሮን ሆናችሁ መላውን ማኅበር በአንድነት ሰብስቡ፤ እዚያም በእነርሱ ሁሉ ፊት ሆነህ ያንን አለት ውሃውን እንዲያወጣ እዘዘው፤ በዚህ ዐይነት ከአለቱ ውስጥ ውሃ ታወጣላቸዋለህ፤ እንዲሁም እነርሱና እንስሶቻቸውም ጠጥተው ይረካሉ።”
እነሆ፥ እኔ ለንስሓ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፤ እርሱ ከእኔ እጅግ ይበልጣል፤ እኔ የእግሩን ጫማ እንኳ ለመሸከም የተገባሁ አይደለሁም።
እኔ ራሴ ለባለ ሥልጣኖች ታዛዥ ስሆን፥ ከእኔ በታች የማዛቸው ወታደሮች አሉኝ፤ ከእነርሱ አንዱን ‘ሂድ!’ ስለው ይሄዳል፤ ሌላውንም ‘ና!’ ስለው ይመጣል፤ አገልጋዬም ‘ይህን አድርግ!’ ስለው ያደርጋል።”