ማቴዎስ 7:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ቃሌን ሰምቶ በሥራ ላይ የማያውለው ግን፥ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራ ሞኝ ሰውን ይመስላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ቃሌን ሰምቶ በተግባር የማያውለው ግን ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራን ሞኝ ሰው ይመስላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህን ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሁሉ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራ ሰነፍ ሰውን ይመስላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሰው ሁሉ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራ ሰነፍ ሰውን ይመስላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህንም ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሰው ሁሉ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራ ሰነፍ ሰውን ይመስላል። |
ጥበበኞቻችሁ ኀፍረት ደርሶባቸዋል፤ በወጥመድ ተይዘውም ግራ ገብቶአቸዋል፤ እነርሱ ቃሌን ትተዋል፤ ታዲያ ምን ዐይነት ጥበብ ሊኖራቸው ይችላል?
ቃሌን ሰምቶ የማይፈጽም ግን ያለ መሠረት ቤቱን በዐፈር ላይ የሠራ ሰውን ይመስላል፤ ጐርፍ መጥቶ ያንን ቤት በገፋው ጊዜ ወዲያውኑ ወደቀ፤ አወዳደቁም እጅግ ታላቅ ሆነ።”
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘የአንተ ቤተሰብና የቀድሞ አባትህ ቤተሰብ ለዘለዓለም ያገለግሉኝ ዘንድ ቃል ገብቼ ነበር፤ አሁን ግን እንዲህ አይሆንም፤ የሚያከብሩኝን አከብራለሁ የሚንቁኝም ይናቃሉ።