ማቴዎስ 28:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠባቂዎቹ መልአኩን ከመፍራት የተነሣ በመንቀጥቀጥ እንደ በድን ሆኑ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠባቂዎቹ መልአኩን ከመፍራት የተነሣ ተንቀጠቀጡ፤ እንደ በድንም ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱን ከመፍራት የተነሣ ጠባቂዎቹ ተንቀጠቀጡ፤ እንደ ሞተ ሰው ሆኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠባቆቹም እርሱን ከመፍራት የተነሣ ተናወጡ፤ እንደ ሞቱም ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጠባቆቹም እርሱን ከመፍራት የተነሣ ተናወጡ እንደ ሞቱም ሆኑ። |
ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ በእግሩ ሥር ወደቅኩ፤ እርሱ ግን ቀኝ እጁን በላዬ ጭኖ እንዲህ አለኝ፤ “አትፍራ፤ የመጀመሪያውና የመጨረሻው እኔ ነኝ፤