ማቴዎስ 27:65 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጲላጦስም “እነሆ፥ የሚጠብቁ ወታደሮች አሉአችሁ፤ ሂዱና በምታውቁት ዐይነት አስጠብቁ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጲላጦስም፣ “ጠባቂዎች አሏችሁ፤ ሄዳችሁ በምታውቁት መንገድ አስጠብቁ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጲላጦስም “ጠባቂዎች አሉላችሁ፤ ሄዳችሁ እንደምታውቁት አስጠብቁ፤” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጲላጦስም “ጠባቆች አሉአችሁ፤ ሄዳችሁ እንዳወቃችሁ አስጠብቁ፤” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጲላጦስም፦ ጠባቆች አሉአችሁ፤ ሄዳችሁ እንዳወቃችሁ አስጠብቁ አላቸው። |
ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ ሄደው እንዳይሰርቁትና ለሕዝቡም ‘እነሆ፥ ከሞት ተነሥቶአል’ እንዳይሉ መቃብሩ እስከ ሦስት ቀን ድረስ እንዲጠበቅ እዘዝ፤ አለበለዚያ የኋለኛው ማሳሳት ከመጀመሪያው ይልቅ የባሰ ይሆናል።”