መግደላዊት ማርያምና ሌላይቱ ማርያም፥ እዚያ በመቃብሩ ፊት ለፊት ተቀምጠው ነበር።
በዚህ ጊዜ ማርያም መግደላዊትና ሌላዋ ማርያም ከመቃብሩ ትይዩ ተቀምጠው ነበር።
እዚያም መግደላዊት ማርያምና ሌላይቱ ማርያም በመቃብሩ ፊት ለፊት ተቀምጠው ነበር።
መግደላዊት ማርያምም ሁለተኛይቱም ማርያም በመቃብሩ አንጻር ተቀምጠው በዚያ ነበሩ።
ከእነርሱም መካከል መግደላዊት ማርያም፥ የያዕቆብና የዮሴፍ እናት ማርያም የዘብዴዎስ ልጆች እናት ይገኙባቸው ነበር።
ሰንበት ካለፈ በኋላ ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን (እሑድ) ጠዋት፥ በማለዳ መግደላዊት ማርያምና ሌላይቱ ማርያም መቃብሩን ለማየት ሄዱ።