La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 27:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚሁም ዓይነት የካህናት አለቆች ከሕግ መምህራንና ከሽማግሌዎች ጋር እንዲህ እያሉ ያፌዙበት ነበር፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የካህናት አለቆችም ከኦሪት ሕግ መምህራንና ከሽማግሌዎች ጋራ ሆነው እያሾፉበት እንዲህ ይሉ ነበር፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዲሁም ደግሞ ሊቃነ ካህናት፥ ከጻፎችና ከሽማግሌዎች ጋር እያፌዙ እንዲህ አሉት፦

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እንዲሁም ደግሞ የካህናት አለቆች ከጻፎችና ከሽማግሎች ጋር እየዘበቱበት እንዲህ አሉ

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንዲሁም ደግሞ የካህናት አለቆች ከጻፎችና ከሽማግሎች ጋር እየዘበቱበት እንዲህ አሉ፦

Ver Capítulo



ማቴዎስ 27:41
12 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ቢመረምራችሁ አንዳች መልካም ነገር ያገኝባችኋልን? ሰዎችን እንደምታሞኙ እግዚአብሔርንም ማሞኘት የምትችሉ ይመስላችኋልን?


በእኔ መከራ ተደስተው ትኲር ብለው በንቀት የሚመለከቱኝ ሁሉ ይፈሩ፤ ግራም ይጋቡ፤ በእኔ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ ሁሉ ኀፍረትንና ውርደትን ይልበሱ።


ጌታ የሠራዊት አምላክ አገሪቱን በሞላ ለማጥፋት መወሰኑን ስለ ሰማሁ ማፌዝ ይቅርባችሁ፤ አለበለዚያ እስራታችሁ ይጠብቅባችኋል።


በሕዝቦች ዘንድ በጣም ለተናቅህና ለተጠላህ፥ ለገዢዎችም አገልጋይ ለሆንክ ለአንተ፥ አዳኙ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ነገሥታት ሲያዩህ ይነሡልሃል፤ ልዑላንም ይሰግዱልሃል፤ ይህም የሚሆነው በመረጠህ በታማኙ በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ምክንያት ነው።”


ሦስቱ እረኞች እኔን ስላስቈጡኝና ስለ ጠሉኝ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አስወገድኳቸው።


“አንተ ቤተ መቅደስን የምታፈርስና በሦስት ቀን የምትሠራው! እስቲ ራስህን አድን! የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ እስቲ ከመስቀል ውረድ!” በማለት ያላግጡበት ነበር።


“ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ግን ማዳን አይችልም! እርሱ የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ እስቲ አሁን ከመስቀል ይውረድ፤ እኛም እንመንበት!


እርሱ ለአሕዛብ ተላልፎ ይሰጣል፤ እነርሱም ያፌዙበታል፤ ይሰድቡታል፤ ይተፉበታል።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ሊይዙት የመጡትን የካህናት አለቆች፥ የቤተ መቅደስ የዘብ አዛዦችንና የሕዝብ ሽማግሌዎችንም እንዲህ አላቸው፦ “እኔን እንደ ወንበዴ ልትይዙ ሰይፍና ዱላ ይዛችሁ መጣችሁን?


ሕዝቡ ቆሞ ይመለከት ነበር፤ የአይሁድ አለቆችም “ሌሎችንስ አዳነ እንግዲህ እርሱ የተመረጠው የእግዚአብሔር መሲሕ ከሆነ እስቲ ራሱን ያድን!” እያሉ ያፌዙበት ነበር።