አቤሴሎምና እስራኤላውያን በሙሉ “ከአኪጦፌል ምክር ይልቅ የሑሻይ ምክር ይበልጣል” አሉ፤ በአቤሴሎም ላይ ጥፋት ይመጣበት ዘንድ እግዚአብሔር የአኪጦፌል መልካም ምክር ተቀባይ እንዳይኖረው አደረገ።
ማቴዎስ 2:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህ ብሎም ወደ ቤተልሔም ላካቸው፦ “ሂዱና፤ ስለ ሕፃኑ በጥንቃቄ መርምሩ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ፥ እኔም ሄጄ እንድሰግድለት መጥታችሁ ንገሩኝ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠቢባኑንም ወደ ቤተ ልሔም ልኮ፣ “ሂዱና ሕፃኑን ፈልጉ፤ እኔም ደግሞ ሄጄ እንድሰግድለት፣ እንዳገኛችሁት ወደ እኔ ተመልሳችሁ የት እንዳለ ንገሩኝ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህ ብሎም ወደ ቤተልሔም ላካቸው፦ “ሂዱ፤ ስለ ሕፃኑ በጥንቃቄ መርምሩ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔ ደግሞ መጥቼ እንድሰግድለት ንገሩኝ” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ቤተ ልሔምም እነርሱን ሰድዶ “ሂዱ፤ ስለ ሕፃኑ በጥንቃቄ መርምሩ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔ ደግሞ መጥቼ እንድሰግድለት ንገሩኝ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ቤተ ልሔምም እነርሱን ሰድዶ፦ ሂዱ፥ ስለ ሕፃኑ በጥንቃቄ መርምሩ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔ ደግሞ መጥቼ እንድሰግድለት ንገሩኝ አላቸው። |
አቤሴሎምና እስራኤላውያን በሙሉ “ከአኪጦፌል ምክር ይልቅ የሑሻይ ምክር ይበልጣል” አሉ፤ በአቤሴሎም ላይ ጥፋት ይመጣበት ዘንድ እግዚአብሔር የአኪጦፌል መልካም ምክር ተቀባይ እንዳይኖረው አደረገ።
ስለዚህ እርስዋ “በእነዚያ ነቢያት ላይ ያደረግኸውን እኔም ነገ ልክ በአሁኑ ሰዓት በአንተ ላይ ሳላደርግብህ ብቀር አማልክት በሞት ይቅሠፉኝ!” ስትል ወደ ኤልያስ የዛቻ መልእክት ላከች።
በንጉሥ ሄሮድስ ዘመን፥ በይሁዳ ምድር በምትገኝ በቤተልሔም ከተማ ኢየሱስ በተወለደ ጊዜ፥ የከዋክብት ተመራማሪዎች ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
እነርሱም የንጉሡን ቃል ከሰሙ በኋላ፥ ወጥተው ሄዱ፤ እነሆ! በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ በነበረበት ቦታ ላይ እስኪቆም ድረስ፥ እፊት እፊታቸው እየሄደ ይመራቸው ነበር።