ማቴዎስ 2:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ራሔል ለልጆችዋ ስታለቅስ፥ የዋይታና፥ የመራራ ለቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ልጆችዋም በሕይወት ስለሌሉ ለመጽናናት እምቢ አለች።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የልቅሶና የታላቅ ዋይታ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች፤ መጽናናትም እንቢ አለች፤ ልጆቿ ዐልቀዋልና።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የልቅሶና የብዙ ዋይታ፥ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ የሉምና መጽናናትን እምቢ አለች።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ልቅሶና ብዙ ዋይታ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ መጽናናትም አልወደደችም፤ የሉምና።” |
በዚህ ጊዜ አባታቸው “ልጆቼን ሁሉ እንዳጣ ትፈልጋላችሁን? ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ለመውሰድ ትፈልጋላችሁ፤ በዚህ ሁሉ መከራ የምሠቃየው እኔ ነኝ!” አለ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የዋይታና የመራራ ለቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ ታለቅሳለች፤ ልጆችዋ በሕይወት ስለሌሉ መጽናናትን እምቢ አለች።
ምጥ የያዛት ሴት የምታሰማውን ጩኸት የመሰለ ድምፅ ሰማሁ፤ የመጀመሪያ ልጅዋን የምትወልድ በካር ሴት የምታሰማውን ድምፅ የመሰለ ኡኡታም አዳመጥኩ፤ ይህም ድምፅ ኢየሩሳሌም ትንፋሽ አጥሮአት እጅዋን ዘርግታ “ወዮልኝ! ጠፋሁ! እነሆ ሊገድሉኝ መጡ!” እያለች የምታሰማው ጩኸት ነበር።
ያም እጅ የብራናውን ጥቅል ፈቶ በፊቴ ዘረጋው፤ እርሱም በሁለት በኩል ጽሑፍ ያለበት መሆኑን አየሁ፤ በእርሱም ላይ የለቅሶ፥ የሐዘንና የዋይታ ቃሎች ተጽፈውበት ነበር።
በዚያ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ስለ ልጅትዋ ያለቅሱ! ዋይ ዋይም ይሉ ነበር። ኢየሱስ ግን “አታልቅሱ፤ ልጅትዋ አንቀላፍታለች እንጂ አልሞተችም፤” አላቸው።
ከዚህ በኋላ ስመለከት አንድ ንስር በሰማይ መካከል እየበረረ በታላቅ ድምፅ “የቀሩት ሦስቱ መላእክት የእምቢልታቸውን ድምፅ በሚያሰሙበት ጊዜ በምድር ላይ ለሚኖሩ ሰዎች ወዮላቸው! ወዮላቸው! ወዮላቸው!” እያለ ሲጮኽ ሰማሁ።