ማቴዎስ 19:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደቀ መዛሙርቱም “የባልና የሚስት ሁኔታ እንዲህ ከሆነ አለማግባት የተሻለ ነው” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደቀ መዛሙርቱም፣ “የባልና የሚስት ጕዳይ እንዲህ ከሆነ አለማግባት ይሻላል” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደቀ መዛሙርቱም “የባልና የሚስት ግንኙነት እንዲህ ከሆነስ መጋባት ጥሩ አይደለም” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደቀ መዛሙርቱም “የባልና የሚስት ሥርዐት እንዲህ ከሆነ መጋባት አይጠቅምም፤” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደቀ መዛሙርቱም፦ የባልና የሚስት ሥርዓት እንዲህ ከሆነ መጋባት አይጠቅምም አሉት። |
እንደእነዚህ ያሉት ሰዎች ጋብቻን ይከለክላሉ፤ የሚያምኑና እውነትን የሚያውቁ ሰዎችም እርሱን እያመሰገኑ እንዲመገቡት እግዚአብሔር የፈጠረላቸውን ምግብ “አትብሉ” እያሉ ይከለክላሉ።