ካህኑም መርምሮት ቊስሉ ያለበት ቦታ ከሌላው የሰውነቱ ቆዳ ይልቅ ጐድጒዶ ቢገኝና በቈዳው ላይ ያለውም ጠጒር ወደ ነጭነት ቢለወጥ እርሱም በእባጭ የተጀመረ የሥጋ ደዌ በሽታ ስለ ሆነ ርኩስ መሆኑን ያስታውቅ።
ማቴዎስ 12:45 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ፥ ርኩሱ መንፈስ ይሄድና ከእርሱ ይብስ የከፉትን ሌሎች ሰባት አጋንንት ይዞ ይመጣል። እነርሱም ቀድሞ የጋኔኑ ቤት ወደ ነበረው ሰው ልብ ገብተው አብረው በዚያ ይኖራሉ። ስለዚህ የዚያ ሰው የኋለኛው ሁኔታ ከመጀመሪያው ይልቅ የከፋ ይሆናል። በዚህ ክፉ ትውልድ ላይ የሚሆነው ይህንኑ የመሰለ ነገር ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በኋላ ሄዶ ከርሱ የከፉ ሌሎች ሰባት ክፉ መናፍስት ይዞ ይመጣል፤ ገብተውበትም በዚያ ይኖራሉ። ለዚያም ሰው ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው ሁኔታ የከፋ ይሆናል። በዚህ ክፉ ትውልድም ላይ እንዲሁ ይሆንበታል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያ ይሄድና ከእርሱ የከፉ ሰባት ሌሎች አጋንንትን ከእርሱ ጋር ይዞ ይመጣል፤ ገብተውም በዚያ ይኖራሉ፤ የሰውየው መጨረሻ ከፊተኛው ይልቅ የከፋ ይሆናል። ለዚህም ክፉ ትውልድ ደግሞ እንዲሁ ይሆንበታል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያ ወዲያ ይሄድና ከእርሱ የከፉትን ሰባት ሌሎችን አጋንንት ከእርሱ ጋር ይወስዳል፤ ገብተውም በዚያ ይኖራሉ፤ ለዚያም ሰው ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው ይብስበታል። ለዚህ ክፉ ትውልድ ደግሞ እንዲሁ ይሆንበታል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያ ወዲያ ይሄድና ከእርሱ የከፉትን ሰባት ሌሎችን አጋንንት ከእርሱ ጋር ይወስዳል፥ ገብተውም በዚያ ይኖራሉ፤ ለዚያም ሰው ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው ይብስበታል። ለዚህ ክፉ ትውልድ ደግሞ እንዲሁ ይሆንበታል። |
ካህኑም መርምሮት ቊስሉ ያለበት ቦታ ከሌላው የሰውነቱ ቆዳ ይልቅ ጐድጒዶ ቢገኝና በቈዳው ላይ ያለውም ጠጒር ወደ ነጭነት ቢለወጥ እርሱም በእባጭ የተጀመረ የሥጋ ደዌ በሽታ ስለ ሆነ ርኩስ መሆኑን ያስታውቅ።
“እናንተ ግብዞች፥ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን! ወዮላችሁ! አንድን ሰው የእምነታችሁ ተከታይ ለማድረግ በባሕርና በየብስ ትዞራላችሁ፤ ባስገባችሁትም ጊዜ፥ ከእናንተ በሁለት እጥፍ ይብስ ለገሃነም የተዘጋጀ ታደርጉታላችሁ!
እናንተ ዕውሮች መሪዎች! ከምትጠጡትም ሁሉ እንደ ትንኝ ትንሽ የሆነችውን ነገር አጥልላችሁ ትጥላላችሁ፤ እንደ ግመል ትልቅ የሆነውን ነገር ግን ትውጣላችሁ!
ከዚህ በኋላ ሄዶ ከእርሱ ይብስ የከፉ ሌሎች ሰባት አጋንንት ይዞ ይመጣል፤ ቀድሞ እርሱ በነበረበት ቤትም ገብተው በዚያ ይኖራሉ፤ የዚያም ሰው የመጨረሻ ሁኔታ ከመጀመሪያው ይልቅ የባሰ ይሆናል።”
የእኛ ውጊያ ከሰዎች ጋር ሳይሆን በዚህ በጨለማ ዘመን ከሚሠሩት ገዢዎች፥ ከባለ ሥልጣኖችና ከዚህ ዓለም ኀይሎችና ይህም ማለት በሰማይ ካሉት ከርኩሳን መናፍስት ሠራዊት ጋር ነው።