ማቴዎስ 12:42 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የደቡብ ንግሥት የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳርቻ ስለ መጣች በፍርድ ቀን ከዚህ ዘመን ትውልድ ጋር ተነሥታ በእርሱ ላይ ትፈርድበታለች፤ አሁን ግን ከሰሎሞን የሚበልጥ እዚህ አለ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በፍርድ ዕለት የደቡብ ንግሥት ከዚህ ትውልድ ጋራ ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳርቻ መጥታለችና። እነሆ፤ ከሰሎሞን የሚበልጥ እዚህ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የደቡብ ንግሥት በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳርቻ መጥታለችና፤ እነሆ ከሰሎሞን የሚበልጥ እዚህ አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፤ እነሆም ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፥ እነሆም፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ። |
እነሆ የጠየቅኸውን አደርጋለሁ፤ እንዲያውም ማንም ሰው ከዚህ በፊት ካገኘውና ወደ ፊትም ሊያገኘው ከሚችለው የሚበልጥ ጥበብንና አስተዋይነትን እሰጥሃለሁ፤
እስራኤላውያን ይህን የፍርድ ውሳኔ በሰሙ ጊዜ ሰሎሞን የሕዝብ ጉዳዮችን በትክክለኛ ፍርድ የሚወስንበትን ጥበብ እግዚአብሔር የሰጠው መሆኑን ስለ ተገነዘቡ ታላቅ አክብሮት ሰጡት።
ስለዚህ ክፉውንና በጎውን በመለየት ሕዝብህን በትክክለኛ ፍርድ ለመምራት የሚያስችለኝን ጥበብ ስጠኝ፤ ይህ ካልሆነ ግን ታላቅ ሕዝብህን እንዴት ልመራ እችላለሁ?”
እግዚአብሔር አስቀድሞ የሰጠውን የተስፋ ቃል በመጠበቅ ለሰሎሞን ጥበብን ሰጠው፤ በኪራምና በሰሎሞን መካከል ሰላም ስለ ነበረ ሁለቱም የጋራ ስምምነት ውል አደረጉ።
የነነዌ ከተማ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ዘመን ትውልድ ጋር ተነሥተው በእርሱ ላይ ይፈርዱበታል፤ የነነዌ ሰዎች የዮናስን ስብከት በሰሙ ጊዜ በኃጢአታቸው ተጸጽተው ንስሓ ገብተዋልና። አሁን ግን ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ።
ጴጥሮስ ገና ይህን ሲናገር ሳለ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ ከደመናውም ውስጥ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት!” የሚል ድምፅ መጣ።
‘እርሱን ሰምተን እንታዘዘው ዘንድ ከባሕር ማዶ ተሻግሮ ማን ሊያመጣልን ይችላል?’ ብለህ እንዳትጠይቅ፥ እርሱ የሚገኘው ከባሕር ማዶ አይደለም።