ማቴዎስ 10:37 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ፥ የእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ፥ የእኔ ሊሆን አይገባውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከእኔ ይልቅ እናቱን ወይም አባቱን የሚወድድ ለእኔ ሊሆን አይገባም፤ ከእኔ ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድድ ለእኔ ሊሆን አይገባም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔም ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ |
ማንም ነቢይ ነኝ ብሎ ቢነሣ የወለዱት አባቱና እናቱ በእግዚአብሔር ስም ሐሰትን ስለ ተናገርክ መሞት አለብህ ይሉታል፤ ትንቢትም ሲናገር ወላጆቹ ወግተው ይገድሉታል።
“ወደ እኔ የሚመጣ ሁሉ አባቱንና እናቱን፥ ሚስቱንና ልጆቹን፥ ወንድሞቹንና እኅቶቹን፥ የራሱንም ሕይወት እንኳ ከእኔ አብልጦ የሚወድ ከሆነ የእኔ ደቀ መዝሙር ሊሆን አይችልም።
ይህንንም ያደረገው ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩ፥ እንዲሁም ወልድን እንዲያከብሩ ነው፤ ወልድን የማያከብር፥ ወልድን የላከውን አብን አያከብርም።
ነገር ግን ልብሳቸውን ያላረከሱ በሰርዴስ ጥቂት ሰዎች ከአንተ ጋር አሉ፤ እነርሱ ነጭ ልብስ መልበስ የሚገባቸው ስለ ሆኑ ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ።
በትእዛዜ መሠረት የሚቀርብልኝን መሥዋዕትና ቊርባን ለምን ታዋርዳላችሁ? ልጆችህ ለመሥዋዕት ከሚቀርበው ምርጥ የሆነውን እየወሰዱ በመብላት ይወፍሩ ዘንድ እነርሱን ከእኔ ይበልጥ የምታከብራቸው ለምንድነው?’