በዚህም ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ አካዝያስ በሰማርያ ቤተ መንግሥቱ ሳለ ከሰገነቱ ላይ ወድቆ በብርቱ ስለ ቈሰለ ታሞ ነበር፤ እርሱም “እኔ ከዚህ ሕመም እድን ወይም አልድን እንደ ሆነ በፍልስጥኤም የዔክሮን ከተማ አምላክ የሆነውን ብዔልዜቡልን ጠይቃችሁልኝ ኑ” ብሎ መልእክተኞቹን ላከ።
ማቴዎስ 10:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ተማሪ እንደአስተማሪው፥ አገልጋይም እንደ ጌታው ከሆነ ይበቃዋል። የቤቱን ጌታ ‘ብዔልዜቡል’ ብለው ከጠሩት ቤተሰቦቹንማ ከዚህ በከፋ ስም እንዴት አይጠሩአቸውም! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደቀ መዝሙር መምህሩን፣ ባሪያም ጌታውን ከመሰለ ይበቃዋል። ባለቤቱን ‘ብዔልዜቡል’ ካሉት፣ ቤተ ሰዎቹንማ እንዴት አብልጠው አይሏቸውም! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደቀመዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባርያም እንደ ጌታው ከሆነ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔልዜቡል ካሉት፥ ቤተሰቦቹንማ እንዴት ከዚህ የበለጠ አይሉአቸው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው! |
በዚህም ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ አካዝያስ በሰማርያ ቤተ መንግሥቱ ሳለ ከሰገነቱ ላይ ወድቆ በብርቱ ስለ ቈሰለ ታሞ ነበር፤ እርሱም “እኔ ከዚህ ሕመም እድን ወይም አልድን እንደ ሆነ በፍልስጥኤም የዔክሮን ከተማ አምላክ የሆነውን ብዔልዜቡልን ጠይቃችሁልኝ ኑ” ብሎ መልእክተኞቹን ላከ።
እነርሱም “አዎ፥ እንችላለን፤” አሉ። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “በእርግጥ እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ፤ እኔም የምጠመቀውን ጥምቀት ትጠመቃላችሁ፤
ከኢየሩሳሌም የወረዱ የሕግ መምህራን፥ “እርሱ ብዔልዜቡል አለበት! አጋንንትንም የሚያወጣው በዚሁ የአጋንንት አለቃ በሆነው በብዔልዜቡል አማካይነት ነው!” እያሉ አወሩ።
ስለዚህ ሰይጣን እርስ በርሱ የሚለያይ ከሆነ የእርሱ መንግሥት እንዴት ጸንቶ መቆም ይችላል? እናንተ ግን ‘እርሱ አጋንንትን የሚያስወጣ በብዔልዜቡል ነው፤’ ትሉኛላችሁ።
አይሁድ እንዲህ አሉት፦ “ጋኔን እንዳለብህ አሁን ዐወቅን፤ አብርሃም እንኳ ሞቶአል፤ ነቢያትም ሞተዋል፤ አንተ ግን ‘ቃሌን የሚጠብቅ አይሞትም’ ትላለህ፤