በሦስተኛው ወር ገደማ ሰዎች “ምራትህ ትዕማር የዝሙት ሥራ ፈጸመች፤ ከዚህም የተነሣ ፀንሳለች” ብለው ለይሁዳ ነገሩት። ይሁዳም “ወደ ውጪ አውጥታችሁ በእሳት አቃጥላችሁ ግደሉአት” አለ።
ማቴዎስ 1:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እጮኛዋ ዮሴፍ ደግ ሰው ስለ ነበረ፥ ማርያምን በሰው ፊት ሊያጋልጣት አልፈለገም፤ ስለዚህ በስውር ሊተዋት አሰበ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕጮኛዋ ዮሴፍ ጻድቅ ሰው ስለ ነበርና ማርያምን በሰው ፊት ሊያጋልጣት ስላልፈለገ በስውር ሊተዋት ወሰነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጮኛዋ ዮሴፍ ጻድቅ ስለ ነበረ ሊያጋልጣት አልፈለገም፥ በስውርም ሊተዋት አሰበ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ። |
በሦስተኛው ወር ገደማ ሰዎች “ምራትህ ትዕማር የዝሙት ሥራ ፈጸመች፤ ከዚህም የተነሣ ፀንሳለች” ብለው ለይሁዳ ነገሩት። ይሁዳም “ወደ ውጪ አውጥታችሁ በእሳት አቃጥላችሁ ግደሉአት” አለ።
“አንድ ሰው ልጃገረድ የሆነች አገልጋዩን ለሌላ ሰው ቊባት ትሆን ዘንድ ለመሸጥ ካስማማ በኋላ ገዢው ገንዘቡን ከፍሎ ከመጨረሱ በፊት ሻጩ ከልጃገረዲቱ ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት ቢያደርግ ሁለቱም ይቀጣሉ፤ ሆኖም እርስዋ ገና ነጻ ያልወጣች አገልጋዩ ስለ ሆነች የሞት ቅጣት አይፈጸምባቸውም።
ሄሮድስ በመጀመሪያ ዮሐንስ ጻድቅና ቅዱስ መሆኑን ስለሚያውቅ ይፈራውና ይጠብቀውም ነበር። ሄሮድስ የዮሐንስን ንግግር በሰማ ቊጥር ይታወክ ነበር፤ ይሁን እንጂ በደስታ ይሰማው ነበር።
በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም ሕይወቱን ለእግዚአብሔር የሰጠ ጻድቅ ሰው ነበር፤ የእስራኤልን የመዳን ተስፋ ይጠባበቅ ነበር፤ መንፈስ ቅዱስም በእርሱ ላይ ነበር።
እነርሱም “እኛ የመጣነው ከመቶ አለቃው ከቆርኔሌዎስ ዘንድ ነው፤ እርሱ የአይሁድ ሕዝብ ሁሉ የሚያከብረው እግዚአብሔርን የሚያመልክ ደግ ሰው ነው፤ አንተን ወደ ቤቱ አስጠርቶ የምትለውን እንዲሰማ ቅዱስ መልአክ ገልጦ ነግሮታል” አሉት።
በነጋም ጊዜ የደረሱበትን ቦታ አላወቁትም፤ ነገር ግን የአሸዋ ዳርቻ ያለውን የባሕር ሰርጥ አዩ፤ የሚቻል ቢሆን መርከቡን ወደዚያ በመግፋት ወደ ዳር ለማውጣት አሰቡ።