ማርቆስ 6:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሄሮድስ ግን ይህን ሁሉ ሰምቶ፦ “ይህ እኔ አንገቱን ያስቈረጥኩት ዮሐንስ ነው፤ እነሆ! እርሱ ከሞት ተነሥቶአል፤” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሄሮድስ ነገሩን ሲሰማ ግን፣ “እኔ ራሱን ያስቈረጥሁት ዮሐንስ ከሙታን ተነሥቷል!” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሄሮድስ ነገሩን ሲሰማ ግን፥ እኔ ራሱን ያስቆረጥሁት ዮሐንስ ከሙታን ተነሥቷአል አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሄሮድስ ግን ሰምቶ “እኔ ራሱን ያስቈረጥሁት ዮሐንስ ይህ ነው፤ እርሱ ከሙታን ተነሥቶአል፤” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሄሮድስ ግን ሰምቶ፦ እኔ ራሱን ያስቈረጥሁት ዮሐንስ ይህ ነው እርሱ ከሙታን ተነሥቶአል አለ። |
አገልጋዮቹን፥ “ይህ መጥምቁ ዮሐንስ ነው፤ እርሱ ከሞት ተነሥቶአል፤ እነዚህ ድንቅ ነገሮች በእርሱ አማካይነት የሚደረጉት ስለዚህ ነው” አላቸው።
ሄሮድስም በበኩሉ “እኔ የዮሐንስን ራስ አስቈርጬ ነበር፤ ታዲያ፥ ይህን ሁሉ ነገር ያደርጋል እየተባለ የሚነገርለት እርሱ ማን ነው?” ይል ነበር። ሊያየውም ይፈልግ ነበር።