“አሁንም እኔ ልዑል እግዚአብሔር ለእናንተ ለእስራኤላውያን የምላችሁ ይህ ነው፤ በክፉ ሥራችሁ እያንዳንዳችሁን እቀጣለሁ፤ ስለዚህ ከምታደርጉት ክፋት ተመለሱ፤ አለበለዚያ ኃጢአታችሁ ያጠፋችኋል።
ማርቆስ 6:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተላኩትም ከዚያ ወጥተው፥ ሰዎች ሁሉ ንስሓ እንዲገቡ አስተማሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ከዚያ ወጥተው፤ ሰዎች ንስሓ እንዲገቡ ሰበኩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ከዚያ ወጥተው፤ ሰዎች ንስሓ እንዲገቡ ሰበኩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወጥተውም ንስሐ እንዲገቡ ሰበኩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወጥተውም ንስሐ እንዲገቡ ሰበኩ፥ ብዙ አጋንንትንም አወጡ፥ |
“አሁንም እኔ ልዑል እግዚአብሔር ለእናንተ ለእስራኤላውያን የምላችሁ ይህ ነው፤ በክፉ ሥራችሁ እያንዳንዳችሁን እቀጣለሁ፤ ስለዚህ ከምታደርጉት ክፋት ተመለሱ፤ አለበለዚያ ኃጢአታችሁ ያጠፋችኋል።
ኢየሱስ እነዚህን ትእዛዞች ለዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ከሰጠ በኋላ ያን ቦታ ትቶ በአቅራቢያው ወደሚገኙት ከተሞች ሊሰብክና ሊያስተምር ሄደ።
ሂዱ፤ ‘እኔ የምፈልገው ምሕረትን እንጂ መሥዋዕትን አይደለም’ ተብሎ የተጻፈው ምን ማለት እንደ ሆነ መርምራችሁ አስተውሉ። እኔ የመጣሁት ጻድቃንን ሳይሆን ኃጢአተኞችን ወደ ንስሓ ለመጥራት ነው” አላቸው።
እንዲሁም የነነዌ ከተማ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው በእርሱ ላይ ይፈርዱበታል፤ የነነዌ ሰዎች የዮናስን ስብከት በሰሙ ጊዜ በኃጢአታቸው ተጸጽተው ንስሓ ገብተዋል፤ ነገር ግን እነሆ፥ ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ።”
ንስሓ መግባት ከማያስፈልጋቸው ዘጠና ዘጠኝ ደጋግ ሰዎች ይልቅ ንስሓ በሚገባ አንድ ኃጢአተኛ ምክንያት በሰማይ እንዲሁ ደስታ ይሆናል እላችኋለሁ።”
እነርሱም ይህንን በሰሙ ጊዜ የሚመልሱትን አጥተው ዝም አሉ፤ “እንግዲህ እግዚአብሔር ለአሕዛብም ለአዲስ ሕይወት የሚያበቃቸውን ንስሓ ሰጥቶአቸዋል፤” በማለትም እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፤ “ንስሓ ግቡ፤ ኃጢአታችሁም ይቅር እንዲባልላችሁ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የእግዚአብሔር ስጦታ የሆነውን መንፈስ ቅዱስንም ትቀበላላችሁ፤
ነገር ግን አስቀድሜ በደማስቆ ያሉት ሰዎች፥ ቀጥሎም በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ምድር ሁሉ ያሉት እንዲሁም አሕዛብ ጭምር ንስሓ ገብተው ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ አስተማርኳቸው፤ ንስሓ መግባታቸውን የሚያመለክት ነገር እንዲያደርጉም አስተማርኳቸው።