ማርቆስ 4:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘሪው ቃልን ይዘራል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዘሪው ቃሉን ይዘራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘሪው ቃሉን ይዘራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘሪው ቃሉን ይዘራል። ቃልም በተዘራበት በመንገድ ዳር የሆኑት እነዚህ ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘሪው ቃሉን ይዘራል። ቃልም በተዘራበት በመንገድ ዳር የሆኑት እነዚህ ናቸው፥ |
በመንገድ ዳር የወደቀው ዘር የሚያመለክተው፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት ቃል ሰምቶ የማያስተውለውን ሰው ነው፤ ወዲያውኑ ሰይጣን መጥቶ በልቡ የተዘራውን ቃል ይወስድበታል፤
ቃሉ በተዘራ ጊዜ በመንገድ ዳር የወደቀው ዘር የሚያመለክተው ቃሉን በሰሙ ጊዜ ወዲያውኑ ሰይጣን መጥቶ በልባቸው የተዘራውን ቃል የሚወስድባቸውን ሰዎች ነው።