ማርቆስ 3:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዙሪያው ተቀምጠው ወደነበሩት እየተመለከተ፥ “እነሆ! እናቴና ወንድሞቼ እነዚህ ናቸው! አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዙሪያው ወደ ተቀመጡትም በመመልከት፣ እንዲህ አለ፤ “እናቴና ወንድሞቼ እነዚህ ናቸው! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዙሪያው ተቀምጠው ወደ ነበሩትም እየተመለከተ፥ “እነሆ! እናቴና ወንድሞቼ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዙሪያው ተቀምጠው ወደ ነበሩትም ተመለከተና “እነሆ እናቴ ወንድሞቼም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዙሪያው ተቀምጠው ወደ ነበሩትም ተመለከተና፦ እነሆ እናቴ ወንድሞቼም። |
ኢየሱስ “ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሂጂና ‘እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ፥ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዐርጋለሁ ብሎአል’ ብለሽ ንገሪያቸው” አላት።
ይህም የሆነበት ምክንያት አስቀድሞ ያወቃቸው ልጁን እንዲመስሉና ልጁም ከብዙ ወንድሞች መካከል በኵር እንዲሆን እግዚአብሔር አስቀድሞ ስለ ወሰነ ነው።