ዝናው በሶርያ አገር ሁሉ ስለ ተሰማ፥ ሰዎች በልዩ ልዩ በሽታና ደዌ የሚሠቃዩትን፥ ርኩሳን መናፍስት ያደሩባቸውን፥ የሚጥል በሽታ ያለባቸውንና ሽባዎችንም ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።
ማርቆስ 2:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሽባውን፥ ‘ኃጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል፤’ ከማለትና፥ ‘ተነሥተህ አልጋህን ተሸከምና ሂድ!’ ከማለት የትኛው ይቀላል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሽባውን፣ ‘ኀጢአትህ ተሰርዮልሃል’ ከማለትና፣ ‘ተነሥተህ ዐልጋህን ተሸክመህ ሂድ’ ከማለት የቱ ይቀልላል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሽባውን ‘ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል፤’ ከማለትና ‘ተነሣ አልጋህንም ተሸከምና ሂድ፤’ ከማለት የቱ ይቀላል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሽባውን ‘ኀጢአትህ ተሰረየችልህ፤’ ከማለት ወይስ ‘ተነሣ አልጋህንም ተሸከምና ሂድ፤’ ከማለት ማናቸው ይቀላል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሽባውን፦ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ ከማለት ወይስ፦ ተነሣ አልጋህንም ተሸከምና ሂድ ከማለት ማናቸው ይቀላል? |
ዝናው በሶርያ አገር ሁሉ ስለ ተሰማ፥ ሰዎች በልዩ ልዩ በሽታና ደዌ የሚሠቃዩትን፥ ርኩሳን መናፍስት ያደሩባቸውን፥ የሚጥል በሽታ ያለባቸውንና ሽባዎችንም ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።
በዚያም ሰዎች በአልጋ ላይ የተኛ አንድ ሽባ ይዘው ወደ እርሱ መጡ። እርሱም እምነታቸውን አይቶ፥ ሽባውን፥ “ልጄ ሆይ! አይዞህ፤ ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል” አለው።