ማርቆስ 2:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም በአረጀ የወይን ጠጅ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን የወይን ጠጁ አቁማዳውን ያፈነዳዋል፤ የወይን ጠጁም ይፈስሳል፤ አቁማዳውም ከንቱ ይሆናል። ስለዚህ ለአዲስ የወይን ጠጅ አዲስ አቁማዳ ያስፈልገዋል፤” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም አዲስ የወይን ጠጅ በአሮጌ አቍማዳ የሚያስቀምጥ የለም፤ ይህ ከተደረገማ የወይን ጠጁ አቍማዳውን ያፈነዳዋል፤ የወይን ጠጁም አቍማዳውም ይበላሻሉ። ስለዚህ አዲስ የወይን ጠጅ መቀመጥ ያለበት በአዲስ አቍማዳ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ የወይን ጠጁ አቁማዳውን ያፈነዳል፤ የወይኑም ጠጅ ይፈሳል፤ አቁማዳውም ይጠፋል፤ አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ያኖራሉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ የወይን ጠጁ አቁማዳውን ያፈነዳል፤ የወይኑም ጠጅ ይፈሳል፤ አቁማዳውም ይጠፋል፤ አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ያኖራሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ የወይን ጠጁ አቁማዳውን ያፈነዳል የወይኑም ጠጅ ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ያኖራሉ። |
እንዲሁም በአረጀ የውሃ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር ማንም የለም፤ ይህ ቢደረግ ግን፥ አቁማዳው ይፈነዳል፤ የወይን ጠጁም ይፈስሳል፤ አቁማዳውም ተበላሽቶ ከጥቅም ውጪ ይሆናል። ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ማኖር ይገባል፤ በዚህም ዐይነት፥ ሁለቱም በደኅና ተጠብቀው ይኖራሉ።”
“ባረጀ ልብስ ላይ አዲስ ዕራፊ የሚጥፍ የለም፤ ይህ ቢደረግ ግን፥ አዲሱ ዕራፊ አሮጌውን ልብስ በመሸምቀቅ ይቀደዋል፤ ቀዳዳውም ከበፊቱ የባሰ ይሆናል።
እነዚህንም የወይን አቁማዳዎች በሞላናቸው ጊዜ ገና አዲስ ነበሩ፤ አሁን ግን የተቀደዱ መሆናቸውን ተመልከቱ! ከጒዞው ርቀት የተነሣ እነሆ፥ ልብሳችንም ጫማችንም አልቆአል።”